ጤና ይስጥልኝ
የአንድ የመንግሥት ሠራተኛ ሥራው የሚቋረጥበትን ሁኔታ ‘’የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010’’ ተደንግጎ የምናገኝና ስለዚሁ የሚከተለዉን እንበል ::


መልካም ምንባብ፡-
ከአዋጁ አንቀጽ 83 እና በተከታታዮቹ እንደምንመለከተው የመንግሥት ሠራተኛው ሥራዉን የአንድ ወር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ በሕመም ምክንያት፣ በችሎታ ማነስ ፣ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት፣ በሠራተኛ ቅነሳ ፣በዲስፕሊን ምክንያት፣ በዕድሜ (በጡረታ) እና በሞት ምክንያት ሥራው ሊቋረጥ እንደሚችልና የአገልግሎት የምሥክር ወረቀት እና በቅነሳ ሥራው የተቋረጠ እንደሁኔታው ክፍያ እንደሚያገኝ ግንዛቤ እንያዝበት ፡፡
ፈጠሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !!!
ደረጀ ማርቆስ
የካቲት 2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment