🏗️በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ ለሠራተኞች ደህንነት በቁም ነገር እናስባለን?

🏛ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ፣ ጋዜቦ ከደምበል ጀርባ በሚገኝ የግንባታ ሳይት ላይ ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል።

🥲ይህ አሳዛኝ ክስተት ሁላችንን ለአንድ ጥያቄ ያነሳሳናል።

🦺 በእውነት በግንባታ ሥራዎቻችን ውስጥ ለሠራተኞች ደህንነት በቂ ትኩረት እንሰጣለን?

🏗️ የደህንነት ጥንቃቄ የዕለት ተዕለት የሥራ ባህላችን ነው?

👷‍♂️ ሠራተኞችስ ለራሳቸውና ለባልደረቦቻቸው ደህንነት ምን ያህል ትኩረት ይሰጣሉ?

🚥ይህ ማንንም ለመውቀስ ሳይሆን እንደ ግንባታ ዘርፍ ተወያይተን ለመማርና ለመሻሻል የተነሳ ጥያቄ ነው።

💬 እናንተ ምን ትላላችሁ? በኢትዮጵያ የግንባታ ሳይቶች የሠራተኞችን ደህንነት በበቂ ሁኔታ እየጠበቅን ነው?

@etconp

Comments

Be the first to add a comment