👉abRen ተመልሷል!

🌟​በዚህ ጊዜ "Architecture, Unfiltered" በሚል መርሃ-ግብር፤ ራሔል ቤላቸው (ከስዊድን) እና ራሔል ሻውል (ከኢትዮጵያ) ከቡድኖቻቸው ጋር በመሆን ተገናኝተው በኪነ-ሕንፃ ሙያ ላይ ግልጽ ውይይት የሚያደርጉበትን መድረክ ይዘውላችሁ ቀርበዋል።

☄ሁለቱ ነዳፊዎች በተለያዩ መልክአ-ምድር፣ ባህል እና የሥራ አካባቢዎች ውስጥ የሃያ ዓመታት የሙያ ልምዳቸውን ያካፍላሉ።

🔆​ይምጡና በውይይቱ ላይ ይሳተፉ፤ ልምዶችን ይካፈሉ፣ ጥያቄዎችን ያንሱ፣ እንዲሁም ከውድቀት እስከ ስኬት፣ ከተማሩአቸው ትምህርቶች እስከ አቋም ማላላት (compromise) እና በመካከሉ ባሉት የኪነ-ሕንፃ ሙያ እውነታዎች ላይ አብረው ያሰላስሉ።

• ​ቀን፦ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 15, 2026)
• ​ሰዓት፦ ከቀኑ 10:30 እስከ ምሽቱ 1:30
• ​ቦታ፦ ክሬቲቭ ሀብ / Creative Hub (አሮጌው ፖስታ ቤት፣ ፒያሳ፣ አዲስ አበባ)
​ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡና ቦታዎትን ይያዙ ። እዚያ እንገናኝ!

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScUrrcmvrdWVKUILL2XfJlbI4wJmDeHY9NBY8TbB22xCCLTfA/viewform
​
(abRen በእውቋ ነዳፊ በራሔል ሻውል የሚመራ ወጣት ነዳፊዎችን ለማብቃት ተልእኮ ያለው እንቅስቃሴ ነው)

Via abRen

@etconp

Comments

Be the first to add a comment