👉በግንባታ ዘርፉ የተሰማሩ አካላት ያላቸው የሥራ ፍላጎት አነስተኛ መሆን ዘርፉን ለሙስና እያጋለጠ ነው ተባለ

🚧የግንባታ ዘርፉን ለሙስና ከሚያጋልጡት ምክንያቶች ውስጥ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ አካላት ለሥራው ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ መሆኑ እንደሆነ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ፤ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ያለባቸው የእውቀት ማነስና የውጪ ምንዛሬ እጥረት ለዘርፉ እድገት ችግር መሆኑን ተናግረዋል።

የግንባታ ዘርፉ ለሙስና ከሚጋለጡት መካከል የሚጠቀስ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው፤ "ይህም የሆነበት ምክንያት ለሚሰራው ሥራ በሙሉ ፍላጎት ማገዝ የሚችሉበት አቅም እየተፈጠረ ባለመሆኑ ነው" ብለዋል። በዚህም በሙስናና ተያያዥ ምክንያቶች የግንባታው ዘርፍ በሙሉ አቅሙ በአግባቡ እየተሰራበት አለመሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያሉትን ችግሮች በሙሉ አስወግዶ፤ ዘርፉ እንዲያድግ ከማድረግ አንፃር የተለያዩ አሰራሮችን እየተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተያያዘም ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የጥሬ እቃ ወይም የግብዓት የአቅም ችግር እንደሌለባት የገለጹት ሥራ አስፈፃሚው፤ እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆኑ ግብዓቶች ስለመኖራቸው ተናግረዋል።

ነገር ግን ግብዓቶችን ከመጠቀም አንፃር ውስንነቶች መኖራቸውን አንስተው፤ የግንባታ ግብዓት አቅርቦትን በሀገር ውስጥ ለመተካት በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የግንባታ ዘርፉ የሕንጻ ግንባታ፣ የመንገድ ሥራ፣ የውሀ ሥራዎችና ሌሎች የግንባታ ሥራዎችን የሚያካትት ሲሆን፤ ከፍተኛ ሀብት የሚፈስበት እንደመሆኑ መጠን ለሙስናና ብልሹ አሰራሮች ተጋላጭ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡

Via አሐዱ ሬዲዮ

@etconp

Comments

Be the first to add a comment