🧱የብሎኬት ግንብ (Block Work) ሲገነባ መረሳት የሌለባቸው ወሳኝ የሳይት ህጎች!
ግንብ በሚገነባበት ወቅት ጥራቱን እና ቀጥታነቱን ለመጠበቅ በምስሉ ላይ እንደሚታየው የክር መመሪያ (Alignment Line/String) እና የሞርታር (Mortar) ውፍረት ትልቅ ሚና አላቸው።
በሳይት ላይ የብሎኬት ስራን ስንቆጣጠር ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
1️⃣ የክር መመሪያ (Alignment & Plumb Line): ብሎኬቱ ወደ ጎን እንዳይዛነፍ እና ወደ ላይ ቀጥ ብሎ እንዲወጣ በክር እና በስፒሪት ሌቭል (Spirit Level) ዘወትር ማረጋገጥ።
2️⃣ የሞርታር ውፍረት (Mortar Joint Thickness): በብሎኬቶች መካከል ያለው የሲሚንቶ ውህድ ውፍረት ከ10-15 ሚ.ሜ (1.0 - 1.5 cm) መብለጥ ወይም ማነስ የለበትም።
3️⃣ ብሎኬቱን ማርከስ (Wetting Blocks): ብሎኬቶች ደረቅ ከሆኑ የሞርታሩን እርጥበት ስለሚመጡት ከመደርደራቸው በፊት በቂ ውሃ ማግኘት አለባቸው።
4️⃣ የማሰሪያ ብረት (Wall Ties/Stiffeners): ግንቡ ከኮለም (Column) ጋር የሚገናኝበት ቦታ ላይ በጥንካሬ እንዲያያዝ የማሰሪያ ብረቶችን ወይም ዶወል (Dowels) መጠቀም።
5️⃣ የቀን ግንባታ ከፍታ (Maximum Lift Height): በአንድ ቀን ከ1.2 እስከ 1.5 ሜትር በላይ አለመገንባት—ከስር ያለው ሞርታር ሳይደርቅ በክብደት እንዳይዛነፍ።
በእናንተ ሳይት ላይ ለብሎኬት ግንብ ጥራት ከሁሉ በላይ ትኩረት የምትሰጡት ለየትኛው ነው?
💡 ተመሳሳይ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችን Follow ያድርጉ
👇https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934@etconp