በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1) መሠረት አንድ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውሉ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

ሀ) ሠራተኛው የሥራ ሰዓት ለማክበር የማይችልባቸው ሁኔታዎች ተብለው በኅብረት ስምምነት በሥራ ደንብ ወይም በሥራ ውሉ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ውጭ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ በጠቅላላው ለስምንት ጊዜ የስራ ሰዓት አለማክበር፤
ለ) በአዋጁ ከተመለከቱ እረፍቶች እና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ ለአምስት ቀናት ከስራ መቅረት፤
ሐ) በሥራው ላይ የማታለል ተግባር መፈፀም፤
መ) የራሱን ወይም የሌላ ሰው ብልጽግናን በመሻት በማንኛውም የአሠሪው ንብረት ወይም ገንዘብ አለአግባብ መጠቀም፤
ሠ) ሠራተኛው ሥራውን ለመሥራት ችሎታ እያለው የሥራ ውጤቱ ባለማቋረጥ በኅብረት ስምምነት ወይም በሥራ ደንቡ ወይም በሁለቱ ወገኖች መግባባት ከተወሰነው የምርት ጥራትና መጠን በታች ሲሆን፤
ረ) እንደጥፋቱ ክብደት በሥራው ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ መሆን፤
ሰ) በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትና በጥፋቱም ምክንያት ለያዘው ሥራ ብቁ ሆኖ አለመገኘት፤
ሸ) በአሠሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
በ) በሠራተኛው ላይ ከሰላሳ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእሥራት ፍርድ ተወስኖበት ከሥራ ሲቀር፤
ተ) ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ ያስችላሉ ተብለው በኅብረት ስምምነት የተወሰኑ ሌሎች ጥፋቶችን መፈፀም፡፡ ናቸው

ፌናን ተጊበሉ
ታህሳስ 11/2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment