🌱«ደህና እደሩ» ብሎ የተኛ ሁሉ በእርግጥ የተኛ ይመስላችኋልን?! ዉሸት ነው።ዱንያ ስንቱን አድክማለች መሰላችሁ።

አንዳንዱ ዓፊያ ርቆት ይገላበጣል፣ሌላውን ትዝታ ወስዶት ያንገላተዋል፣አንዳንዱን #ናፍቆት ወጥሮት ያስከንፈዋል፣ሌላው ብቸኝነት ወስዶ ያስባንነዋል፣ትራስ ላይ ያረፈ ጭንቅላት ሁሉ አይተኛም፣ያረፈ ገላ ሁሉ አያርፍም፣የነገ ዉሎው የሚያሳስበው አለ፣የወደፊት ዕጣው የሚያስጨንቀው ብዙ ነው፣የሁኔታውን መጨረሻ የሚያሰላስል በርካታ ነው፣የእዳ መአት የሚያስተክዘው መዓት ነው፣የተጋደመ ሁሉ አይተኛም።

ጨለማ ብርድልብስ ነው። በውስጡም  የሚወራ ነገር ጉድ ነው።ምሽት ፀጥታ ነው፣ የናፍቆት ጓዙ በርካታ ነው።

ወዳጄ ሁሉን ነገር ነፍስህን ለፈጠራት ጌታ አስረክበህ ተኛ።ከተሸከምነው ይከብደናል፣ ለሱ ስንሰጥ ግን ይቀለናል።


╭┈───────ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰┈➤@ᵗᵉʷʰᵉᵈᵃⁿᵈˢᵘⁿᵃ   🌱] ❞​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•

Comments

Be the first to add a comment