💫በአማካሪነት ሙያ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የሚጠቅም መረጃ።
⭐️ግብር ከፋዮች የሚይዟቸው የሒሳብ ሰነዶች።
⏺ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ የሚደረግበት ዓላማ በትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት ግብር ለማስከፈል እና የታክስ ተመላሽን ለመፍቀድ ነው፡፡
❇️ስለሆነም ግብር ከፋዮች የሚከተሉትን የሂሳብ ሰነዶች መያዝ ይኖርባቸዋል:-
👉 ከንግድ ስራው ጋር የተገናኘ በየቀኑ የሚያገኘውን ማንኛውም ገቢ እና ወጪ የሚያሳይ ሰነድ
👉 አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብን የተከተለ የሂሳብ ሰነድ (GAAP/IFRS/ Authorized tax format)
👉 ህጋዊ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ፣
👉 የዱቤ ሽያጭ ደረሰኝ፣
👉 የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ፣
👉 የዴቢት/ክሬድት ሰነድ፣
👉 በኤሌክትሮንክ የመረጃ ማከመቻ መሳሪያ ውስጥ ተከማችቶ የተያዘ፣
👉 ከተከፋይ ሒሳብ ላይ ተቀናሽ የተደረገውን WHT የሚያሳይ ደረሰኝ፣
👉ከግብር ከፋዩ ቅድመ ታክስ ተቀናሽ የተደረገበትን የታክስ መጠን ደረሰኝ፣
👉 ታክስ ከፋዩ ወደ አገር ውስጥ ላስገባው ዕቃ ቀረጥና ታክስ የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ የጉሙሩክ ድክላራስዮን፣ የዕቃ መልቀቂያ ሰነድ፣ የክፍያ ደረሰኝ፣
👉 ታክስ ከፋዩ ወደ አገር ውስጥ ዕቃ ስያስገባ ከCIF ላይ 3% እና በአገር ውስጥ ግብይት ሲያከናውን 2% የተቀነሰበትን ንግድ ትርፍ ታክስ ከዓመታዊ ታክስ ያቀናነሰበትን ሂሳብ የሚያሳይ ዝርዝር ሰንጠረዥ እና ደረሰኝ፡፡
ከ ገቢዎች ሚኒስቴር Facebook ገጽ
@etconp