👉የግድብ (Dam) ንድፍ(design) ደረጃዎች ወይም Steps እንደሚከተለው አሰናድቼ አቅርቤላቹዋለሁ ከወደዳችሁት ሼር አድርጉት

🚧1. የፕሮጀክት መለየት እና የተፈጻሚነት ጥናት (Feasibility Study)

⭐️ዓላማ: ፕሮጀክቱ ቴክኒካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ የሚቻል መሆኑን ለመረጋገጥ።
የፕሮጀክቱን ዓላማ መግለጽ (መስኖ፣ ኃይል ማመንጨት፣ የጎርፍ መቆጣጠር፣ የውሃ አቅርቦት)
የመጀመሪያ የቦታ ምርጫ
ሲቀጥል የሃይድሮሎጂ እና የመሬት ካርታ ጥናት
የወጪ ግምት እና የጥቅም–ወጪ ትንተና
የአካባቢ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ጥናት

🚧2. የቦታ ምርመራ (Site Investigation)

⭐️ዓላማ: የዳሙን ቦታ የአካላዊ ሁኔታ ለመረዳት።

a) የመሬት ካርታ ጥናት (Topographic Survey)
የመሬት ኮንቱር ካርታ ማዘጋጀት
የሬዘርቫር መጠን እና ከፍታ ግንኙነት መወሰን

b) የጂኦሎጂ እና የጂኦቴክኒካል ጥናት
የአፈር እና የድንጋይ አይነት መለየት
የመሠረት የመሸከም አቅም መወሰን
የውሃ መስረቅ (permeability) መለካት
የስንጥቅ እና የድንጋይ ጉድለት መለየት
የውሃ ሹልኪያ ጥናት

🚧3. የሃይድሮሎጂ ትንተና (Hydrological Analysis)

⭐️ዓላማ: የውሃ መጠን እና የጎርፍ መጠን ለመወሰን።

የካችመንት አካባቢ ጥናት
የዝናብ–ፍሰት ትንተና
የንድፍ ጎርፍ መጠን መወሰን
የሬዘርቫር አቅም ትንተና
የደለል (sediment) ጥናት

❇️ዋና ውጤቶች:
መደበኛ የውሃ ደረጃ (NWL)
ከፍተኛ የውሃ ደረጃ (MWL)
የንድፍ ጎርፍ ደረጃ (MFL)

🚧4. የዳም አይነት ምርጫ (Selection of Dam Type)
የሚመረጠው በሚከተሉት መሰረት ነው:

የመሠረት ሁኔታ
የንብረት አቅርቦት
የሸለቆ ቅርጽ
የኢኮኖሚ ሁኔታ

የተለመዱ አይነቶች:
ግራቪቲ ዳም
አርች ዳም
በትረስ ዳም
የአፈር ዳም
የድንጋይ ሙሌት ዳም

🚧5. የሃይድሮሊክ ንድፍ (Hydraulic Design)

⭐️ዓላማ: የውሃ ፍሰትን መቆጣጠር።

የስፒልዌይ ንድፍ
የውሃ መውጫ ንድፍ
የመግቢያ መዋቅር
የውሃ ማስቀየሻ ስራ

🚧6. የመዋቅር ትንተና (Structural / Stability Analysis)

ዳሙ ደህንነቱ እንዲጠበቅ ይህ ይደረጋል።
የሚታሰቡ ጭነቶች:
የራሱ ክብደት
የውሃ ግፊት
የከፍታ ግፊት (uplift)
የደለል ግፊት
የመሬት መንቀጥቀጥ
የንፋስ እና የማዕበል ግፊት
የሚመረመሩ:
መገልበጥ (Overturning)
መንሸራተት (Sliding)
የመሠረት ግፊት
የጭነት ስርጭት

🚧7. የውሃ ሾልኮ ትንተና (Seepage Analysis)

በተለይ ለአፈር ዳም አስፈላጊ ነው።
የውሃ ፍሰት ትንተና
የphreatic line መወሰን
የpiping መከላከል
የሚካተቱ:
ፊልተሮች
ድሬን
cutoff wall

🚧8. የመሠረት ንድፍ (Foundation Design)

ደካማ አካባቢ ማሻሻል
ግራውቲንግ
cutoff trench ንድፍ

🚧9. የሬዘርቫር እና ደለል ትንተና (Reservoir & Sedimentation Analysis)

የደለል መጠን መወሰን
የdead storage ንድፍ
የuseful storage መወሰን

🚧10. የመሬት መንቀጥቀጥ ትንተና (Seismic Analysis)

የመንቀጥቀጥ ጭነት ትንተና
የዳሙ መረጋጋት መርመር

🚧11. የአካባቢ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ጥናት (Environmental & Social Impact)
የአካባቢ ተፅዕኖ
የህዝብ ማፈናቀል ጥናት
የአካባቢ ጥበቃ(ተፅእኖ) ጥናት

🚧12. የግንባታ እቅድ (Construction Planning)
የግንባታ ደረጃዎች
የውሃ መቀየሪያ
የንብረት አቅርቦት
የወጪ ግምት

🚧13. የክትትል እና መለኪያ ንድፍ (Instrumentation & Monitoring)
piezometer
settlement gauge
uplift pressure meter

ዓላማ: የዳሙን ደህንነት መከታተል

Via 𝑬𝒓. 𝑴𝒆𝒌𝒂𝒎𝒖 𝑴𝒐𝒉𝒂𝒎𝒎𝒆𝒅𝒌𝒂𝒎𝒖

🚧የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

Comments

Be the first to add a comment