👉መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፀም ትኩረት መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች

🏛ማንኛውም መኖሪያ ቤት ግዥ ሲፈፅሙ ትኩረት ማድረግ ያለባችሁ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩/ በሁሉ አስቀድሞ ይዞታው ህጋዊ ካርታ (የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት) እና ህጋዊ ፕላን ያለው መሆን አለበት፡፡

፪/ በሻጭ እጅ ያሉ ሰነዶችና በክ/ከተማው በመዝገብ ቤት በሻጭ ስም ያለ የይዞታ ማህደር ጋር ሰነዶች በትዩዩ አንድ አይነት መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡ በተለይም በካርታው ላይ ያለው የካርታ ቁጥርና በክ/ከተማ መዝገብ ቤት ያለው ቀሪ ካርታ ቁጥር ተመሳሳይ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡

፫/  የይዞታ ማህደሩ ከእዳ፣እገዳና ሌሎች ክልከላዎች ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የሊዝ እዳ ገዥው እስከ እዳው መግዛት የሚፈልግ ከሆነ እዳውን ማስተላለፍ ይቻላል፡፡

፬/  ትዳር ያለው ከሆነ ከወሳኝ ኩነት የትዳር ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት፡፡ ትዳር የሌለው ከሆነ ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያስፈልጋል፡፡

፭/  ሕጋዊ የሽያጭ ውል በሰነዶች ምዝገባ/ውልና ማስረጃ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

፮/ በውክልና የሚሻሻጡ ከሆነ ውክልናው ህጋዊ መሆኑን ውክልና ከሰጠው የፍትህ ተቋም ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

፯/ በተጨማሪም በአካል ወደ ሚሸጠው ቤት ሂዶ ቤቱን በአካል ማየትና ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ማለትም ይዞታው ወደ ፊት ለመኖሪያ ወይስ ወደ ንግድ መቀየር ይቻላል የሚለውን ሀሳብና ከግንባታ ከፍታ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን ማማከርና ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment