ጤና ይስጥልኝ
ግለሰቦች ውሃና መብራትን የመሰሉ አገልግሎቶችን ከየተቋማቱ ጋር ባደረጉት ግንኙነት የሚያገኙ ሲሆን ለዛሬው የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ከሚቀርበው አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኛ ያለውን መብት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢነርጂ ደንብ ቁጥር 447/2011 እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም ንባብ፡፡
(ሀ) ከባለፈቃዱ አስተማማኝ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ኤሌክትሪክ የማግኘት፣
(ለ) እንደየአግባቡ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ማናቸውም አቤቱታ በባለሥልጣኑ በሚወጣ የአሰራር ሥርዓት መሠረት ለባለፈቃዱ ወይም ለባለሥልጣኑ የማቅረብ፣ እና
(ሐ) ደረጃውን ባልጠበቀ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ምክንያት በዕቃዎችና መገልገያዎች ላይ ለሚደርስ ማናቸውም ጉዳት ተመጣጣኝ ካሣ የማግኘት


ደረጀ ማርቆስ
ታህሳስ 2013 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment