👉Triaxial Shear Force ምን ማለት ነው❓

🚥የአፈር ወይም የድንጋይ ናሙና ከሦስቱም አቅጣጫዎች ጫና (Pressure) እያረፈበት ባለበት ሁኔታ፣ በውስጡ የሚፈጠረው የመንሸራተት ኃይል ነው።

▶️በተፈጥሮ ውስጥ አፈር ከመሬት በታች ሲሆን ከሁሉም አቅጣጫ በዙሪያው ባለው አፈር ተጨኖ (Confined ሆኖ) ነው የሚኖረው። ይህንን ተፈጥሯዊ ሁኔታ በቤተ-ሙከራ (Lab) ውስጥ ለመምሰል Triaxial Test የሚባል ምርመራ ይደረጋል፦

⏺የከበበ ጫና (Confining Pressure ) የአፈሩ ናሙና ውሃ ባለበት ሲሊንደር ውስጥ ይገባና ከሁሉም አቅጣጫ እኩል የሆነ ፈሳሽ ጫና እንዲያርፍበት ይደረጋል (ይህ አፈሩ ከመሬት በታች ያለውን ሁኔታ ይወክላል)።

🔆ቀጥተኛ ጫና (Axial Load )

⏺በመቀጠል ናሙናው ላይ ከላይ ብቻ ተጨማሪ ኃይል ይጫናል። ውጤቱ (Shear Failure) ከላይ የሚመጣው ጫና እየጨመረ ሲሄድ፣ አፈሩ ጫናውን መቋቋም አቅቶት በሰያፍ (በአግድም አቅጣጫ) ይንሸራተታል። ይህ እንዲንሸራተት የሚያደርገው ኃይል Triaxial Shear Force ይባላል።

☄ለምን ይጠቅማል? (አስፈላጊነቱ)‼️

⏺የሲቪል መሐንዲሶች ይህንን ምርመራ እና ኃይል የሚያጠኑት ለሚከተሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው

1. የሕንፃ መሠረት (Foundation) ጥንካሬን ለማወቅ

2. መሬቱ የተሰራበትን ሕንፃ ክብደት መሸከም ይችል እንደሆነ ወይም አፈሩ ተሸርሽሮ ሕንፃው ሊሰምጥ እንደሚችል ለማረጋገጥ

3. የመሬት መንሸራተትን (Slope Stability) ለመከላከል

4. በተራራማ ቦታዎች ላይ መንገድ ሲሰራ ወይም ግድብ ሲገነባ የመሬት መንሸራተት አደጋ እንዳይከሰት

5. የግድቦች (Dams) እና የመንገዶች ደህንነት ግድቡ የያዘውን ከፍተኛ የውሃ ግፊት አፈሩ መቋቋም መቻሉን ለማረጋገጥ።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment