🍃🕯 ˓٭˛ ،
🌸🌱 ነቢዩሏህ ዮሱፍ ከሁለት ወጣቶች ጋር እስር ቤት ገቡ።ግና ሁለቱም ቀድመዋቸው ወጡ።
ሲወጡ የሱን ነገር ለአለቃቸው እንዲነግሩለት አደራ አላቸው።እነርሱ ግን አደራዉንም እሱንም ረሱ።
~ ሓጃቸዉን ከነርሱ ይልቅ ለአምላካቸው መናገር የነበረባቸው ዩሱፍም ለዓመታት በእስር ቤት ቆዩ።ቀድመዋቸው ከወጡት መካከል አንደኛው አገልጋይ ሆነ።ሁለተኛው በስቅላት ተገደለ።
☞ ዘግይተው የወጡት ዩሱፍ ግን ከግብጽ ሚኒስቴሮች አንዱ ሆኑ።
እናሳ…እናማ…ያንተ/ያንች
ፋይል አልተረሳም።ጌታህም ረሺ አይደለም።ጉዳይህ የዘገየው ለምክንያት ሊሆን ይችላል።በደንብ አብስሎ ሊሰጥህ ይሆናል።
እስቲ አትቸኩል ንጉሥ ትሆን ይሆናል።
ሚኒስቴር ትሆን ይሆናል።ዘግይተህ መድረስህን አትጥላ ወዳጄ።
@tewhedandsuna •┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•