🏗 ለኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች (Contractors) የተዘጋጀ አስፈላጊ መረጃ!

🏛በኢትዮጵያ ወቅታዊ የኮንስትራክሽን ገበያ ውስጥ ጨረታ አሸንፎ ስራ መጀመር ብቻውን ለውጤታማነት በቂ አይደለም።

🔆በርካታ ተቋራጮች በስራ ሂደት ውስጥ ለኪሳራ የሚዳረጉባቸው 3 ዋና ዋና የጨረታ እና የፕሮጀክት ዝግጅት ስህተቶች አሉ።

🚥ዛሬ ከእነዚህ ስህተቶች እንዴት መንቃት እንደምትችሉ በጥቂቱ እናያለን፦

📌 1. የገበያ ዋጋ ንረትን ያላገናዘበ ስሌት (Unrealistic Cost Estimation)

የግንባታ እቃዎች (ሲሚንቶ፣ ብረት፣ አሸዋ፣ ሬንጅ...) ዋጋ በፍጥነት በሚለዋወጥበት ሁኔታ፣ የዛሬውን ዋጋ ብቻ መሰረት አድርጎ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ፕሮጀክት ዋጋ ማስገባት ለትልቅ ኪሳራ ይዳርጋል።

🌟መፍትሄ፦ በስሌትዎ ውስጥ ሁልጊዜም በህግ የተፈቀዱ የዋጋ ማስተካከያ (Price Escalation) ደንቦችን እና የዋጋ ንረት ህዳግ (Inflation Contingency) በስርአቱ ማካተት።

📌 2. የቴክኒክ እና የፋይናንሻል ሰነድ አለመጣጣም (Technical & Financial Mismatch)

አንዳንድ ተቋራጮች ማራኪ የፋይናንሻል ዋጋ ቢያቀርቡም፣ በቴክኒክ ሰነዳቸው ላይ የሚጠየቁትን የባለሙያ ብዛት፣ የስራ ልምድ ወይም የማሽነሪ ዝርዝር ሳያሟሉ በመቅረታቸው ከጨረታ ውጪ (Disqualify) ይሆናሉ።

🌟መፍትሄ፦ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባትዎ በፊት በባለሙያ ሁለት ጊዜ ማጣራት (Cross-check) ማድረግ።

📌 3. የጊዜ ሰሌዳን (Schedule) ማጋነን

አሠሪውን ለማስደሰት ብቻ ሊሳካ የማይችል እጅግ አጭር የማጠናቀቂያ ጊዜ ማስቀመጥ፣ በኋላ ላይ በጥራት ማነስ ወይም በቅጣት (Liquidated Damages) ምክንያት ፕሮጀክቱ አትራፊ እንዳይሆን ያደርጋል።

ጥራት ያለው የጨረታ ዝግጅት እና የፕሮጀክት አስተዳደር የድርጅትዎን ህልውና ይወስናል!

Via Ethio Con

@etconp

Comments

Be the first to add a comment