🐑ኡድሒያ ማረድ የፈለገ

ዛሬ ማክሰኞ (ግንቦት 19/2017) ዙል-ቂዕዳህ 29 ሲሆን ምናልባትም ይህ ወር በ29 ካለቀ ነገ ረቡዕ ዙል-ሒጃህ 1 ስለሚሆን ኡድሒያ የማረድ እቅድ ያለው ሰው ዛሬ ቀን ጸሐይ ከመጥለቋ በፊት ሰውነት ላይ መነሳት ያለባቸው ጸጉሮችንና ጥፍርን ማንሳት ተገቢ ነው።

🤩 ነቢዩ {🤩} በሐዲሣቸው የሚከተለውን ብለዋል፥ "አንዳችሁ ኡድሒያ ለማረድ ካሰበ የዙል-ሒጃህ ወር ከገባ በኋላ እርዱን እስኪፈጽም ድረስ ከጸጉሩና ከጥፍሩ ምንም አይንካ (አያንሳ)"

ይህን ትዕዛዝ እንደ ግዴታ በማየት "ኡድሒያ የሚያርድ ሰው የዙል-ሒጃህ ጨረቃ ከታየበት ጊዜ አንስቶ የዒድ ሰላት ተሰግዶ እስኪታረድ ድረስ ጸጉርና ጥፍርን መቁረጥ ክልክል (ወንጀል) ነው" የሚሉ ሊቃውንት ስላሉ ከወዲሁ ጥፍርንና በሸሪዓህ የሚፈቀድን ጸጉር ማንሳት ይገባል።

NB:ይህ ህግ የሚመለከተው ኡድሒያ የሚያርደውን አባወራ ብቻ ነው።


🌟🔗😊 ᵗᵉʷʰᵉᵈᵃⁿᵈˢᵘⁿᵃ👈🟢🔤
🤩

1 comment

ያለ ተወሂድ ሂዎት ጨለማ ናት ام مريم
ሀ/ና ለ