👉ስድስት የቤት ገዢዎች ኖህ ሪል ስቴት ኃ.የተ.የግ.ማህበር በገባቸው ውል መሰረት ቤቶችን አላስረከበንም በማለት ክሳቸውን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ የፍትሐ ብሔር ችሎት አቅርበዋል።

💫ይህ የህግ ክርክር ያነጣጠረው ኩባንያው እያገነባው በሚገኘው የ'ኖህ ቪክቶሪ አፓርትመንት' ፕሮጀክት ላይ ሲሆን፣ ደንበኞቹ አፓርትመንቶቹ በተባለው ጊዜ አልተላለፉልንም በማለት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።

🚧ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ታትሞ የሚወጣው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ በምስሉ ላይ ይፋ እንዳደረገው መረጃ፣ የክርክሩ ዋነኛ መነሻ የቤቶቹ ርክክብ መዘግየት ብቻ ሳይሆን የቦታ ስፋትን (ካሬን) የተመለከተ ውዝግብ ጭምር ነው።

🪧በተለይም በሰነድ ላይ ተጨማሪ የወለል ስፋት (ካሬ) ሲጨመር ተጨማሪውን የገንዘብ ክፍያ ማን ይሸፍናል የሚለው ጉዳይ በዚህ በሪል ስቴቱ እና በቤት ገዢዎቹ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አቢይ ነጥብ መሆኑ ተጠቁሟል።

Via ዘ-ሐበሻ

@etconp

2 comments

For Fun
muhammed constraction Material Supply
Construction materil materials akrbot