👉እስኪ ዛሬ ደግሞ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ PPA 2011 በመጠቀም እንዴት የጨረታ ዶክመንት  እንደምናዘጋጅ እናያለን

🏷የጨረታ ዶክመንት (Bid document) ሶስት ምዕራፎች እና ዘጠኝ ክፍሎች አሉት እነሱም የሚከተሉት ናቸው፣

✅ምዕራፍ 1. የጨረታ ስርዓቶች(Bidding Procedures)

✴️ክፍል 1.የተጫራቾች መመሪያ (Instructions to Bidders (ITB))
✴️ክፍል 2. የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰነድ(Bid Data Sheet (BDS))
✴️ክፍል 3. የግምገማ መስፈርት (Evaluation and Qualification Criteria (EQC))
✴️ክፍል 4.የጨረታ ቅፆች (Bidding Forms)
✴️ክፍል 5. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ሀገሮች (Eligible Countries)

✅ምዕራፍ 2. የተፈላጊ ሁኔታዎች ሰንጠረዥ(Schedule of Requirements)

✴️ክፍል 6. የተፈላጊ ሁኔታዎች ሰንጠረዥ(Schedule of Requirements including Scope of works, technical specifications, drawings and bill of quantities.)

✅ምዕራፍ 3. ውል (Contract)

✴️ክፍል 7. አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች (General Conditions of Contract (GCC) )
✴️ክፍል 8. ልዩ የውል ሁኔታዎች (Special Conditions of Contract (SCC)) እና
✴️ክፍል 9. ሞዴል ውሎች (Contract Forms) ናቸው::

📜ስለዚህ ጨረታውን ለማዘጋጀት አዘጋጆች ከላይ ከተዘረዘሩት ዉስጥ ክፍል 1 የተጫራቾች መመሪያ እና ክፍል 7 አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች ሳይለወጡ ባሉበት ሁኔታ ጥቅም ላይ ማዋል አለባቸው በ ክፍል 1 እና ክፍል 7 ዉስጥ ሊካተት የሚገባው ዝርዝር ወይም መረጃ  በክፍል 2 የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰነድ እና በ ክፍል 8 ልዩ የውል ሁኔታዎች ዉስጥ በቅደም ትከተል ሊካተት ይችላል:: ሌሎቹን ክፍሎች ግን እንደሚከተለው በማስተካከል መጠቀም ይቻላል::

🚧ክፍል 2.የጨረታ ዝርዝር መረጃ፦በዚህ ክፍል ዉስጥ እንደ የአጫራቹ ማንነት,አድራሻ, ጨረታው ሚገባበት ጊዜ እና ቦታ ሌሎችም እና የምሳሳሉት ዝርዝር ነገሮች የምናስቀምጥበት ነዉ::

🚧ክፍል 3. የግምገማ መስፈርት፦ በዚህ ክፍል ዉስጥ ተጫራቾችን ለመምረጥ የሚሆኑ መስፈርቶች መሞላት ይኖርባቸዋል:: ለምሳሌ ተጫራቾች የሚኖራቸው ማሺኖች (excacator,mixer,dump truck etc.), ባለፉት 5 ወይም 3 አመታት 💯% ያጠናቀቁአቸው ፕሮጀክቶች እና ሌሎችም::

🚧ክፍል 4.የጨረታ ቅፆች፦ በዚህ ክፍል ዉስጥ ያሉ ቅፆች በተጫራቾች የሚሞሉ ናቸው እና ግዥ ፈፃሚው አካል ምንም አይነት ለውጥ ማድረግ የለበትም::

🚧ክፍል 5. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ሀገሮች፦ በዚህ ክፍል ዉስጥ ወጪዎች በመንግስት በሚሸፈን ግዥዎች ላይ እንደ ስታንዳርድ መመሪያ ሃተታ ተቀምጧል::

⏺ግዥው በለጋሾች የግዥ ደንብ መሰረት የሚፈፅም ከሆነ ወይም መንግስት በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ አገሮችን በሚመለከት ማንኛውም የተለየ ወይም ተጨማሪ ሕግ ካወጣ ለውጥ ማድረግ ይችላል::

🚧ክፍል 6. የተፈላጊ ሁኔታዎች ሰንጠረዥ፦ በዚህ ክፍል ዉስጥ ስራውን በተመለከተ ሙሉ ዝርዝር ነገሮች የስራውን ወሰን በሚገባ በሚያሳይ መልኩ መቀመጥ አለበት:: በዉስጡም እንደ scope of works, technical specification, drawings እና  bill of quantity Or activity schedule በሚገባ መካተት አለባቸው::

🚧ክፍል 8. ልዩ የውል ሁኔታዎች በዚህ፦ ክፍል ዉስጥ ለፕሮጀክቱ ልዩ የሆኑ ነገሮች የሚቀመጡበት ነዉ:: ለምሳሌ እንደ liquidated damage፣price adjustment፣defects liability period እና የመሳሰሉት::

🚧ክፍል 9.ሞዴል ውሎች፦ በዚህ ክፍል ያሉት ውሎች የሚሞሉት አሸናፊው ከታወቀ በሁዋላ ቢሆንም ውሉ ምን ይመስላል የሚለውን ቀድመው ተጫራቾች እንዲያውቁት ስለሚጠበቅ ግዥ ፈፃሚ አካላት በዚህ ክፍል ዉስጥ ሊያካትቱት ይገባል::

🔰ስለዚህ ክፍል 1 አና 7ን እንዳለ በመተው እና ሌሎች ክፍሎችን በማስተካከል ማዘጋጀት ይቻላል!

🏷ጥያቄ ካላችሁ comment ላይ አሳውቁን ከወደዱት ደሞ share ያድርጉ

@etconp

4 comments

ሰላም እንዴት ናችሁ
የዋጋ ማስተካከያ /price adjustment @SCC not applicable/allowed…የሚል የውል ሰነድ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም ሀገራዊ የዋጋ ጭማሪ Due to price escalation…በሚል የዋጋ ማስተካከያ የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ተተግብሯል….ስለዚህ ጉዳይ ህጉ ምን ይላል? አመሰግናለሁ
የተሰራ ዶኩመንት ቢያያዝበት መልካም ነው
Please send as full documents.