👉ስለ ኮንስትራክሽን ስዕሎች ማብራሪያ (Construction Drawings Explained) ይፈልጋሉ?

👷‍♂የኮንስትራክሽን ስዕሎች የማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክት ቋንቋ ናቸው። ዲዛይኑን በግልጽ ሁኔታ በማስተላለፍ ፕሮጀክቱ በደህንነት፣ በትክክለኛነት እና በሚፈለገው የጥራት ደረጃ እንዲገነባ ያግዛሉ።

❇️ዋና ዋና የኮንስትራክሽን ስዕሎች/Main Types of Construction Drawings:

✏ፕላን (Plan)

• የሕንፃውን አቀማመጥ፣ መጠኖች፣ Grid Lines፣ ግድግዳዎች፣ አምዶች፣ ክፍተቶች፣ መሳሪያዎች እና የደረጃ መረጃዎችን ያሳያል።

✂️ሴክሽን (Section)

• ሕንፃውን በቁመት ተቆርጦ በሚታይበት መልኩ መሠረት፣ ወለሎች፣ መዋቅራዊ ክፍሎች እና ቁሳቁሶችን ያሳያል።

🪧ኤሌቬሽን (Elevation)

• የሕንፃውን ውጫዊ ገጽታ፣ ከፍታ፣ በሮች፣ መስኮቶች፣ ፊኒሽ እና የጣሪያ ቅርጽን ያሳያል።

📎ዲቴይል (Detail)

• የአስፈላጊ ክፍሎችን፣ ግንኙነቶችን፣ የብረት ዝርዝር፣ ቁሳቁሶችን እና የግንባታ ዘዴዎችን በትልቅ ስኬል ያቀርባል።

🏷ማስታወሻዎች (Notes)

• ደረጃዎች፣ ቴክኒካዊ መስፈርቶች፣ የስህተት ገደቦች፣ የደህንነት መመሪያዎች፣ የግንባታ ቅደም ተከተል እና ልዩ መመሪያዎችን ይይዛሉ።

💫ጥሩ የኮንስትራክሽን ስዕሎች/Why are they important?

✔️ ግራ መጋባትን ይቀንሳሉ/Reduce misunderstandings
✔️ የድጋሚ ሥራን ያስወግዳሉ/ Minimize costly rework
✔️ የፕሮጀክት መዘግየትን ይቀንሳሉ/Prevent construction delays
✔️ የጥራትና የደህንነት ደረጃን ያሻሽላሉ/Improve quality and safety
✔️ የፕሮጀክት ስኬትን ያረጋግጣሉ/Ensure successful project delivery

🔖ግልጽ ስዕሎች + ግልጽ ማስታወሻዎች = ቀላል ግንባታ + የተሻለ የፕሮጀክት ውጤት::

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp

1 comment

ሰላም ለሁላችሁ። እኔ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በEnvironmental Health የተመረቅሁ ፍሬሽ ግራጁዌት ነኝ። በEHS/HSE፣ Environmental Health፣ Safety Officer ወይም ከሙያዬ ጋር የተያያዘ ማንኛውም የስራ እድል ቢኖር እንድታሳውቁኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

በትጋት መስራት፣ መማር እና ከቡድን ጋር በተስማምቶ መስራት ፍላጎት አለኝ። ለማንኛውም ተስማሚ የስራ እድል ብቁ እንደሆንኩ አምናለሁ።

📞 ስልክ፦ 0914963609

ለምታደርጉልኝ ድጋፍና መረጃ ከልብ አመሰግናለሁ።