👉ኢንስቲትዩቱ የኮንስትራክሽን ምህንድስናና ኢንጅነሪንግ ልዕቀት ማዕከል የ3ኛውን ምዕራፍ ግንባታ ውል ስምምነት ተፈራረመ

🏷የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል በሰንዳፋ ከተማ የሚያስገነባውን የልቀት ማዕከል የ3ኛው ምዕራፍ ግንባታ ውል ከሀክኮን ኢንጅነሪንግ ጋር በኢንስቲትዩት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራሪሟል፡፡

በውል ፊርማውም ለልዕቀት ማዕከሉ ሠራተኞችና ሰልጣኞች መኖሪያ የሚውል ሁለት ባለ 5 ፎቅ ህንጻ በ925,828, 095 ብር በሥራ ተቋራጩ የሚገነባ ይሆናል፡፡

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ታምራት ሙሉ ኢንስቲትዩቱ ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ ለመንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ የዘርፉ ተዋናዮች ተግባርን መሠረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንድሁም የዘርፉ ተዋናዮችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንድሆኑ እና የሚመሩትን የግንባታ ፕሮጀክቶችን ውጤታማነታቸውን ባረጋገጠ መልኩ እንድያከናውኑ የሚያግዝ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፈሽናል ስልጠና አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው የፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡

የሀክኮን ኢንጅነሪንግ ባለቤት አቶ አሰግድ ኩራባቸው በበኩላቸው ጨረታው ግልፅና አሳታፊ መሆኑን አመስግነው፣ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመሥራታችን አቅም እንድንፈጥር ያደርገናል ብለዋል፡፡

ግንባታውንም በተቀመጠው ጊዜ መሠረት አጠናቆ እንደሚያሰረክቡ ተናግረዋል፡፡

@etconp

1 comment

Betell
ሰላም ጤና ይስጥልኝ
ፍስሐ የቁፋሮ እና የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢ ነው
+251 95251 2849
+2519 1234 9805