🏘️ አዲስ አበባ በ5 ዓመታት ውስጥ 496 ሺህ 971 ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላለፈች፤ ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ የባንክ ዕዳም ከፍላለች ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ ባለፉት አምስት ዓመታት 496 ሺህ 971 ቤቶችን ገንብቶ ለነዋሪዎች ማስተላለፉን ገለጸ። ከዚህ በተጨማሪም ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ የባንክ ዕዳ መክፈሉን አስታውቋል።

📌 የቤት አቅርቦት አፈጻጸም
በባለፉት አምስት ዓመታት ከተገነቡና ለነዋሪዎች ከተላለፉት ቤቶች መካከል፦

🔵 26,563 የመንግሥት ቤቶች ለልማት ተነሺዎች ተላልፈዋል።

🔵 ከ98 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሁለት ዙር ዕጣ ለቆጣቢዎች ተሰጥተዋል።

🔵 በአሁኑ ወቅት 179,516 ቤቶች በተለያዩ የግንባታ አማራጮች እየተገነቡ ይገኛሉ።

ግንባታዎቹ የ24/7 የሥራ ባህልንና ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እየተፋጠኑ እንደሚገኙ ተገልጿል።

💰 ከ65 ቢሊዮን ብር በላይ የባንክ ዕዳ ተከፍሏል

አስተዳደሩ ለረጅም ዓመታት ሳይከፈል የቆየውን የጋራ መኖሪያ ቤት የባንክ ዕዳ በመክፈል የዕዳ ጫናውን ማቃለሉን ገልጿል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻም 3.18 ቢሊዮን ብር የቦንድ ዕዳ መመለሱን አስታውቋል።

በአስተዳደሩ መረጃ መሠረት፣ ያለፉ የዕዳ ክፍያዎች በቤት ግንባታ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሀብቶችን እንደያዙ ተጠቅሷል።

የባንክ ዕዳው እጅ ባይዝ ኖሮ ተጨማሪ 100 ሺህ ቤቶችን መገንባትና ማስተላለፍ ይቻል ነበር የሚል ግምትም ቀርቧል።

🏗️ በአዲስ አበባ በ21 ሳይቶች 100 ሺህ አዳዲስ ቤቶች እየተገነቡ ነው

መንግሥት በጉባ ብሥራት የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ መርሐ ግብርን በይፋ ማስጀመሩ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ በ21 ሳይቶች እየተገነቡ ካሉት 100 ሺህ ቤቶች፦

▪️ 50 ሺህ ቤቶች በከተማው በጀት፤
▪️ ቀሪዎቹ 50 ሺህ ቤቶች ደግሞ በመንግሥት፣ በግል አጋርነትና በማኅበራት ትብብር እየተገነቡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቱሉ ዲምቱና በአዲስ ከተማ ቅጠል ተራ የቤቶቹን ግንባታ በመጎብኘት የሥራውን አፈጻጸም መመልከታቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንባታው ዓላማ የሕዝቡን የቤት ጫና ማቃለልና ለቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ሁኔታ መፍጠር መሆኑን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤም የቤት ጥያቄን መመለስ የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ አደራና ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፣ በ24/7 የሥራ ባህል በትጋት እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

ከቤት ግንባታ በተጨማሪ አስተዳደሩ ለአቅመ ደካማ ዜጎችና ለልማት ተነሺዎች ቤቶችን በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራትና በምገባ መርሐ ግብሮች የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።

በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማት እንዲሁም በሌሎች የከተማ ልማት ሥራዎች አማካኝነት በመዲናዋ የነበረውን የጎስቋላነት መጠን ከ74 በመቶ ወደ 30 በመቶ ማውረድ መቻሉን ከከተማ አስተዳደሩ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

@etconp

1 comment

አረ ቁጥር እንፍራ ወገን🙆 500,000ቤት🤔