👉አፈርን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት ተጠናቀቀ

💫ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

⏺የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ (ኢ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተጠናው ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው በሐረሪ፣ በድሬዳዋ እና በጅግጅጋ አካባቢዎች የሚገኘውን አፈር ለቤት ግንባታ በሚውል መልኩ ማዘጋጀት ላይ ነው።

⏺ቴክኖሎጂው የተለመደውን ብሎኬት ከመጠቀም ይልቅ፣ በአካባቢው የሚገኘውን አፈር ከትንሽ ሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ደረጃውን የጠበቀ ቤት ለመገንባት የሚያስችል ነው ብለዋል።

⏺በእነዚህ አካባቢዎች ለሚኖሩ ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ ችግርን የሚቀርፍ መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

⏺ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ በሲሚንቶ ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ እንዳይሆኑ በማድረግ የግንባታ ወጪን በእጅጉ እንደሚቀንስም ተገልጿል።

⏺ጥናቱ ሁሉንም የኢንጂነሪንግ መስፈርቶች አሟልቶ በቤተ-ሙከራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት "ለአካባቢያዊ ችግር አካባቢያዊ መፍትሔ" በሚል ስትራቴጂ ለመጨረሻ ማረጋገጫ ለውይይት ቀርቧል።

Via Gazeta +

@etconp

1 comment

እሽ እስኪ በምስል የተደገፈ መረጃ አሳዩን?