👉ተጠባቂው የብድር አቅርቦት መሻሻልና የሪል እስቴት ልማትና ግብይት

❇️በመጪው አዲስ ዓመት የባንክ ብድር አቅርቦት ይሻላል መባሉንና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም 50ቢሊየን ብር ብድር ለዲያስፖራ ማዘጋጀቱንና ብድሩ የቤት ግዢንም  የሚያካትት መሆኑን ሰምተናል።

⏺እነዚህ ዜናዎችን የተመለከተ በሪል እስቴት ዘርፍ ውስጥ ያለ አልሚም ሆነ ቤት ገዢ እንዲሁም የግብይት ባለሙያ ብድር መለቀቁ ለዘርፉ የተሻለ ነገር ያመጣል ብሎ  እየጠበቀ ነው። እንደጥበቃቸው መልካም እንዲሆን እየተመኘሁ የገንዘብ አቅርቦት መሻሻል ልዩ በሆነው የሀገራችን የሪል እስቴት ኢንቨስትመንትና ግብይት ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን አስተዋጽኦና ተጽዕኖ በገባኝ መጠን ካለንበት ተነስቼ ወደ ምንሄድበት  በጥቂቱ ላስቀምጥ።

📍የት ነን?

⏺በሪል እስቴት ግብይት ዑደት መሰረት ግብይቱ አሁን የሚገኘው ውድቀት (recession) በሚባለው ወስት ላይ ይገኛል።

⏺በውድቀት ወቅት መገለጫዎች መሰረት ብዙ ቤቶች የገዢ እጥረት ገጥሟቸዋል፣ ወደ ዘርፉ የሚገቡ አዳዲስ አልሚዎች ቁጥር ቀንሷል፣ ተደጋጋሚ የዋጋ ቅናሾች እየተደረጉ ነው....

📍ወዴት እንሄዳለን?

💫በዘርፉ ተፈጥሯዊ ዑደት መሰረት ቀጣይ ተጠባቂው ወቅት የማገገሚያ (recovery) ወቅት ነው።

⏺ዘርፉን ከውድቀት ወደ ማገገም ለማስገባት ከሚደግፉ ተግባራት አንዱ የገንዘብ አቅርቦት መሻሻል ነው።

⏺ምንም እንኳን የሚለቀቀው ብድር ቀጥታ ለቤት ግንባታና ግዢ ባይሆንም የተለያዩ  የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በማነቃቃት ከስድስት ወራት በኋላ በሪል እስቴት ዘርፍ ላይ ግብይቱን ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።

🎲ነገር ግን የገንዘብ አቅርቦት መሻሻል ብቻውን በሀገራችን ያለውን የሪል እስቴት ግብይት ከውድቀት ወደ ማገገም ሊወስደው አይችልም።

📜ምክንያቶቹ እነሆ:-

፩) የመግዛት አቅም እጅጉን ተዳክሞ መቆየቱ
 
፪) የብድር ወለድ ምጣኔ ከፍተኛ መሆን

፫) የዋጋ ጭማሪ የሚጠበቅ መሆኑ

፬) የመሬት አቅርቦት ቢሻሻልም አሁንም ውድ መሆኑ

፭) የግንባታ ግብዓት ዋጋ እየጨመረ መሄዱ

፮) የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ቢሻሻልም የብር ዋጋ ከሌሎች አንጻር እየቀነሰ መሄድ መቀጠሉ

፯) ገበያው ውስጥ ያሉት ቤቶች ተመሳሳይ/ተቀራራቢ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ዜጎችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው...

🏷ምን ቢደረግ ይበጃል?

🚧በሀገራችን ዘርፉ በቅጡ እንዲያገግምና ዜጎችም የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚከተሉት ቢከወኑ የተሻለ ይሆናል:-

፩) ለቤት ገዢዎች እጅግ በጣም አናስተኛ በሆነ የወለድ ምጣኔ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር ቢመቻች

፪) አናስተኛ ገቢ ላላቸው በዜሮ ወለድ በረጅም ጊዜ የሚከፍሉት የቤት አማራጭ ቢኖር

፫) ለአልሚዎች በጣም አነስተኛ በሆነ ዋጋ መሰረተ ልማት የተሟላለት መሬት በማቅረብ ቀድሞ በተወሰነ ቁርጥ ዋጋ በተገደበ ጊዜ ቤት እንዲያቀርቡ ቢደረግ

፬) በአነስተኛ ዋጋ ቤት ለሚያቀርቡ አልሚዎች ከቀረጥ ነጻ የግንባታ ግብዓት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት

፭) ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ለሚገዙ ዜጎች የተጨማሪ እሴት ታክስና የስም ማዞሪያ ወጪዎች እንዳይከፍሉ ቢደረግ።

፮) ተኪ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በስፋት እንዲመረቱ ቢደረግ

፯) ለሽያጭ ከሚቀርቡ ቤቶች በተጨማሪ ዜጎች በኪራይ ሊገለገሉባቸው የሚችሉ መሰረታዊ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን የሚያሟሉ ቤቶችን  ( core products) በብዛት ገንብቶ ማቅረብ

፰) በከተማችን አስገዳጁ ለአንድ ቤት አንድ መኪና ማቆሚያ መስፈርት በአነስተኛ ዋጋ ቤት ለሚያቀርቡ አልሚዎች ቢቀር/ቢሻሻል

💫ከላይ የተጠቃቀሱትን የመሳሰሉ መፍትሄዎች አብረው ካልቀረቡ በስተቀር የገንዘብ አቅርቦት ብቻውን ዘርፉን ከውድቀት ወደ መረጋጋትና መስፋፋት የሚወስድ ሳይሆን በተቃራኒው ውድቀት ውስጥ ተጨማሪ ጊዜያትን እንዲያሳልፍ የሚያደርግ ነው የሚሆነው።

Via ኢ/ር ደሳለኝ ከበደ የሪል እስቴት ቢዝነስ አማካሪ

@etconp

1 comment

እጅግ በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው ያነሳከው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍልን የሚያሳትፍ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እንዲኖር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይሄንን ሀሳብ ሊጋሩት ይገባል