💭 ኢማሙ በቁኑት ወቅት እንዲህ ሲል፦ አላሁመ-ህዲና ፊመን ሀደይት (አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ ከመራሃቸው ጋር ምራን)
ሲል •
አንተ ምን ትላለህ? ...
አሚን• ኢማሙ፦ ወ ዓፊና ፊመን ዓፈይት (ጤናና ጥንካሬን ከሰጠሃቸው ጋር ስጠን) ሲል
•
አንተ ምን ትላለህ ? ...
አሚን•
እሺ እንዲህ ሲልስ፦ ኢነሁ ላ የዚሉ መን ዋለይት፣ ወላ የዒዙ መን ዓደይት፣ ተባረክተ ረበና ወ ተዓለይት (አንተ የወደድከውና ወዳጅ ያደረግከው ፈጽሞ አይዋረድም፣ አንተ ጠላት ያደረግከውም ፈጽሞ ክብር አያገኝም። ጌታችን ሆይ! አንተ ጥራት ይገባህ፣ ላቅክም ነህ)
ሲል •
አንተ በዚህ ጊዜ ምን ትላለህ?
🪶 ከሱና ጋር በጣም የቀረበው
ዝም ማለት ነው። ነገር ግን "ሱብሃን አላህ" ብትል ይፈቀዳል።
⛔
ነገር ግን... "አሚን" ማለት
አይፈቀድልህም። ምክንያቱም የአሚን ትርጉም "አላህ ሆይ! (ይህንን ዱዓ) ተቀበለን/መልስልን" ማለት ነው።
🪶 ይህ ልክ አንድ ሰው ዱዓ እያደረገ "አላህ ሆይ! ደመናትን የምታንቀሳቅስ፣ የጠላትን ሰራዊት ድል የምታደርግ ሆይ!" ሲል እንደማለት ነው። አይሆንም፣ (እዚህ ላይ) አሚን አትልም። ምክንያቱም የአሚን ትርጉም "አላህ ሆይ! ጸሎቴን መልስልኝ፣ ይሁንልኝ" ማለት ስለሆነ ነው። (እነዚህ ደግሞ የጌታ መገለጫዎች እንጂ ልመናዎች አይደሉም)።
🔵 @TewhedandSuna 🌐
بارك الله فيك
ካጠፋሁ አፉወን