This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💭 ኢማሙ በቁኑት ወቅት እንዲህ ሲል፦ አላሁመ-ህዲና ፊመን ሀደይት (አላህ ሆይ! ቀጥተኛውን መንገድ ከመራሃቸው ጋር ምራን) ሲል

• አንተ ምን ትላለህ? ... አሚን

• ​ኢማሙ፦ ወ ዓፊና ፊመን ዓፈይት (ጤናና ጥንካሬን ከሰጠሃቸው ጋር ስጠን) ሲል

• አንተ ምን ትላለህ ?  ... አሚን

• ​ እሺ እንዲህ ሲልስ፦ ኢነሁ ላ የዚሉ መን ዋለይት፣ ወላ የዒዙ መን ዓደይት፣ ተባረክተ ረበና ወ ተዓለይት (አንተ የወደድከውና ወዳጅ ያደረግከው ፈጽሞ አይዋረድም፣ አንተ ጠላት ያደረግከውም ፈጽሞ ክብር አያገኝም። ጌታችን ሆይ! አንተ ጥራት ይገባህ፣ ላቅክም ነህ) ሲል

• ​አንተ በዚህ ጊዜ ምን ትላለህ?

🪶 ከሱና ጋር በጣም የቀረበው ዝም ማለት ነው። ነገር ግን "ሱብሃን አላህ" ብትል ይፈቀዳል።

⛔ ​ ነገር ግን... "አሚን" ማለት አይፈቀድልህም። ምክንያቱም የአሚን ትርጉም "አላህ ሆይ! (ይህንን ዱዓ) ተቀበለን/መልስልን" ማለት ነው።

🪶​ ይህ ልክ አንድ ሰው ዱዓ እያደረገ "አላህ ሆይ! ደመናትን የምታንቀሳቅስ፣ የጠላትን ሰራዊት ድል የምታደርግ ሆይ!" ሲል እንደማለት ነው። አይሆንም፣ (እዚህ ላይ) አሚን አትልም። ምክንያቱም የአሚን ትርጉም "አላህ ሆይ! ጸሎቴን መልስልኝ፣ ይሁንልኝ" ማለት ስለሆነ ነው። (እነዚህ ደግሞ የጌታ መገለጫዎች እንጂ ልመናዎች አይደሉም)።

🔵 @TewhedandSuna 🌐

18 comments

Show 1 more comment
Iskiyalf yalafal
Amiin malat ayichalim?
رّبّ هب لِی حُکمًا وألحِقنی بِلصَّلِحینَ
በአማርኛ ብተረጉሙልን
እኔስ ተማርኩኝ ያኑሉ ህዝብ ምን ላርገው አሚን ሚለውን እንደ ሀሳብ ኢማሞች ቢናገሩ እኛ ጋር አሚን ይላሉ አብዘሀኞቻቸው ኢማሙ እንዳይሉ አውቆ ይፈጥናል ማለታቸውን አይተዉም አላህ ይዘንልን
Halifa Abdella
ሱብህ ሶላት ላይ በሁለተኛው ረከአ የሚደረገው ዱዓ በፊፁም አለውቅም ምንድነው የሚባለው?
እሺ ኢማሞቹ ለምን ይጠቀሙታል
Iskiyalf yalafal
Iji mansat isa indet yitayal
"ኢነሁ ላየዚህሉ" ሳይሆን "ኢነሁ ላ የዚሉ "በሚል ይስተካከል።
እንም በደን ሁሉም ነገር ለሐይ ርነው
እስከዛሬ እኔም አለቅም ነበረ ጀዛከአሏል ግን ሰዎቹ እያሉነው
ሞቴን አታስረሳኝ
ማስረጃው ምንድነው
ሞቴን አታስረሳኝ
ማስረጃው ምንድነው
ምን ማስረጃ ያስፈልገዋል ይሄ የአላህ ልቅና እየተነሳ አሚን አትበሉ ነው የተባልነው
ሞቴን አታስረሳኝ
°بلال؛؛𝕓𝕚𝕝𝕒𝕝°
ምን ማስረጃ ያስፈልገዋል ይሄ የአላህ ልቅና እየተነሳ አሚን አትበሉ ነው የተባልነው
ሀቢቢ አሚን አትበሉ ከተባለ ማስረጃ መጠየቅ አያስወቅስም
ሞቴን አታስረሳኝ
ሀቢቢ አሚን አትበሉ ከተባለ ማስረጃ መጠየቅ አያስወቅስም
ያ አኺ ፁፉን እኮ ከተረዳህው ለምሳሌ አላህ ብዙ ይረዝቃ አላህ ታላቅ ነው ሲባል አሚን እነሰደማለት ነው

ካጠፋሁ አፉወን
➣𝙮𝙪𝙨𝙧a (يسرا)📚🧕
አሚን አትበሉ ከተባለ ማስረጃ ስጠን ?
➣𝙮𝙪𝙨𝙧a (يسرا)📚🧕
አሚን አትበሉ ከተባለ ማስረጃ ስጠን ?
መጀመሪያ video በደንብ ስሙት አረብኛው ከልገባቹ አማርኛውን በደንብ አንብቡ
አላህሆይ አንተንያስደሰትኩህለትነፍሴንውሰዳት👍👍
ጀዛከላህ