👉የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

💡የድርጅቱ ስም፦ ዳሽ ኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ሀ/የተ/የግ/ማ

🧱የሥራ መደብ፦ የሳይት ሥራ አስኪያጅ

🔑የሥራ ዘርፍ፦ ኮንስትራክሽን የውስጥ ዲዛይን

🗂የትምህርት ደረጃ

- በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት፣ በሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ በአርክቴክቸር ወይም በተዛማጅ ዘርፍ የተመረቀ

🔋የሥራ ልምድ:- በኮንስትራክሽን በውስጥ ዲዛይን የሳይት ሥራዎች ላይ ቢያንስ 2 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው

🖲ዋና ዋና ኃላፊነቶች

1. የኮንስትራክሽን የውስጥ ዲዛይን ሥራዎችን በሳይት ላይ መምራትና መቆጣጠር።
2. ሥራዎች በዲዛይን፣ በዕቅድና በተወሰነው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መከናወናቸውን ማረጋገጥ።
3. የሠራተኞችን፣ የቴክኒሻኖችንና የኮንትራክተሮችን ሥራ ማስተባበርና መከታተል።
4. የሥራ ጥራትን፣ የቁሳቁስ አጠቃቀምንና የወጪ ቁጥጥርን መከታተል።
5. የውስጥ ማጠናቀቂያ ሥራዎችን እንደ ቀለም፣ ሴራሚክ፣ ጣሪያ፣ ካቢኔትና ሌሎች የውስጥ ዲዛይን ሥራዎች በጥራት መከናወናቸውን ማረጋገጥ።
6. የሥራ ቦታ ደህንነትንና ንጽህናን መጠበቅ።
7. የሥራ እድገትን፣ ችግሮችንና የቁሳቁስ ፍላጎትን ለማኔጅመንት ሪፖርት ማድረግ።
8. ከዲዛይነሮች፣ ከኢንጂነሮችና ከደንበኞች ጋር በቅርበት መሥራት።

🎚የሚፈለጉ ችሎታዎች

- ጥሩ የአመራርና የሥራ ማስተባበር ችሎታ።
- የቴክኒክ ስዕሎችንና የውስጥ ዲዛይን ዕቅዶችን የመረዳት ችሎታ።
- የጊዜ፣ የበጀትና የጥራት ቁጥጥር ችሎታ።
- ችግር የመፍታትና በቡድን የመሥራት ችሎታ።

🕹የሥራ ቦታ :- መስቀል ፍላወር ጋዜቦ አደባባይ አብኬም ታወር 1ኛ ፎቅ

🏷ማመልከቻ

📩ተፈላጊውን ብቃትና ልምድ የሚያሟሉ አመልካቾች የሥራ ልምድ ማስረጃና የትምህርት ማስረጃዎችን ቴሌግራም ላይ @AnteNigussHR በመላክ ማመልከት ይችላሉ።

📲ለበለጠ መረጃ በ 0984217657 ይደውሉ

@etconp

1 comment

Giddumaan Jireenya
Structural construction work levev v