👉‎የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 26 የፊውቸር ፕሮጀክት ማናጀሮችን አስመረቀ።

💫‎በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ áŠ•áŒáŒáˆ­ ያደረጉት  የኮርፖሬሽኑ áˆĽáˆŤ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ኮርፖሬሽኑ የፕሮጀክት ማኔጅመንት የስልጠና ማዕከልን በማቋቋም በዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ያደረገው አስተዋጽዖ ፕሮጀክትን በጥራት እና በጊዜ ከመፈጸም ባሻገር በኮንስትራክሽን ዘርፉ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ  ደረጃ ተወዳዳሪ ያደርጋል ብለዋል።

‌‎የኮርፖሬሽኑ ዋና ሼል አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በኮርፖሬሽኑ ኮንስትራክሽን ፕሮፌሽናልስ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ባለፉት 6 ወራት የተሰጠውን የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና የተከታተሉ 26 የፊዩውቸር ፕሮጀክት ማናጀሮች መመረቃቸውን ገልጸው ተመራቂዎች በቀጣይ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማናጅመንት ሥራዎች ላይ በመሰማራት የኮርፖሬሽኑን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድጉ ተናግረዋል፡፡

‌‎ተመራቂዎች በ27 የተለያዩ የፕሮጀክት ማኔጅመንት የስልጠና ሞጅሎች ላይ 30 በመቶ የንድፈ ሀሳብ እና 70 በመቶ የመስክ የተግባር ስልጠና የወሰዱ ናቸው።

‌‎በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች፣ የኮርፖሬሽኑ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አመራሮች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

@etconp

2 comments

Dear Engineers would you support me by giving job opportunity for site Engineer or office with medium level.