👉የግንባታ ጥራትን ማስጠበቅ የህልውና ጉዳይ ነው

ግንባታዎች የግብዓቶች መዋቅራዊና ውህዳዊ ቅንብሮች ብቻ ሳይሆኑ የአዕምሮና የስነልቦና ውህዳዊ ቅንብር የሆኑ ውቅሮች ናቸው፡፡
የሚገነቡትም ደመ-ነፍሳዊ ለሆነ የወዲያውነት እርካታ ሳይሆን ለትውልድ ተሻጋሪ፣ ዘመናትን ዘላቂ የሆኑ የጥበብ አሻራዎች ናቸው፡፡

ይህ የሚሆነው ደግሞ የኢንዱስትሪው ቤተሰቦች የግንባታ ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ የጋራ ጽኑ እምነት ሲኖራቸው ነው፡፡

ምክንያቱም በግንባታው ዘርፍ ውስጥ ፈታኝ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል ለአደጋ ተጋላጭነቱ አንዱና ግንባር ቀደሙ በመሆኑ ነው፡፡

ስለሆነም ጥራታቸውን የጠበቁ ግንባታዎችን መገንባት የዛሬው እና የነገው ትውልድ የደህንነት ዋስትና፣ እንዲሁም የመኖር ተስፋና ራዕይ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ የግንባታ ህጎች፣ ኮዶች እና ስታንዳርዶችን ማስጠበቅ ፣ ማክበር እና ማስከበር ቁልፍ ጉዳይ ያደርገዋል፡፡

የግንባታ ጥራትን ማስጠበቅ የሀገር፣ የሰው እና የፍጥረታት ህልውና እንዲሁም የትውልድ እምነት ጭምር ነው፡፡

ይህንን ታላቅ ሀገራዊ እና የትውልድ አደራ እና እምነትን ለመወጣት ጥራቱን የጠበቀ የፕሮጀክት ቀረጻ፣ ጥራቱን የጠበቀ የዲዛይን ስራ፣ ጥራቱን የጠበቀ የፕሮጀክት አመራር፣ ጥራቱን የጠበቀ የግንባታ ሂደት፣ጥራቱን የጠበቀ የቁጥጥር ስርአት፣ ጥራቱን የጠበቀ የሙያ ስነምግባር … ወዘተ ይጠይቃል፡፡

በመሆኑም የግንባታ ደህንነት ዋስትና የሆነውን ጥራትን ማስጠበቅና ማረጋገጥ የዘርፉ ቤተሰቦች፣ ባለድርሻ አካላት ሞራላዊ፣ሙያዊ እና ሕጋዊ ኃላፊነት ነው፡፡ መሰረቶቹም ሕጎች፣ ኮዶችና ስታንዳርዶች ናቸው፡፡

ግንባታዎችን በጥራት፣ በብቃት እና በታማኝነት የመገንባት ባህል የትውልድን እና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ የዘርፉ ቤተሰቦች ኢትዮጵያን

በጋራ እንገንባ! ... በብቃት፣ በጥራት እና በታማኝነት!

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን

@etconp

1 comment

ተደጋፊ ነኝ