👉በአገራችን የግንባታ ኮንትራት ስርዓት መሠረት (በተለምዶ በ Public Procurement and Property Authority መመሪያዎች እና በ Ethiopian Public Procurement Proclamation No. 649/2009 የመሠረተ ልማት) በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ የስራ መጠን ለውጦች፣ ክፍያዎች እና የኮንትራክተር አፈፃፀምን ለመቆጣጠር ብዙ የኮንትራት ቃላት ይጠቀማል።

🌟ከእነዚህ ዋና ዋና ቃላት የሚከተሉት ናቸው።

1. ኦሚሽን (Omission)

ትርጉም:- ኦሚሽን ማለት በኮንትራቱ ውስጥ የተጠቀሰ አንድ የስራ ክፍል ወይም እቃ ከፕሮጀክቱ ውስጥ መወገድ ማለት ነው።

ዓላማ:-
-  የፕሮጀክቱ ዲዛይን ሲቀየር
-  የበጀት ጉዳይ ሲኖር
-  አንዳንድ ስራዎች አስፈላጊ ካልሆኑ

ባህሪያት:-
- በ Variation Order ይፈፀማል
- ኮንትራክተሩ ለተወገደው  ሾል ክፍያ አይጠይቅም
- የኮንትራት ዋጋ ይቀንሳል

ምሳሌ:-
10 km የውሃ መስመር ለመጫን ተወስኖ ነበር። በኋላ 2 km አስፈላጊ አይደለም ተብሎ ከፕሮጀክቱ ተወገደ።

2.
አዲሽን (Addition / Extra Work)
ትርጉም:-
አዲሽን ማለት ከመጀመሪያ ኮንትራት በኋላ የሚጨመር አዲስ ስራ ወይም የስራ መጠን መጨመር ነው።

ዓላማ
- ዲዛይን እንዲሟላ ያደርጋል
-  የፕሮጀክቱ ጥራት እንዲሻሻል ይጠቅማል

ባህሪያት
-  በኢንጅነር ወይም በባለቤት ይፀድቃል
- በ Variation Order ይመዘገባል
- ኮንትራክተሩ ተጨማሪ ክፍያ ይቀበላል

የክፍያ መንገዶች:-
-  የኮንትራቱን ዋጋ መጠቀም
-  አዲስ ዋጋ መወሰን
-  Daywork መጠቀም

3.
ቫሪዬሽን ኦርደር (Variation Order)
ትርጉም:-
ቫሪዬሽን ኦርደር ማለት በኮንትራቱ ውስጥ ያለውን የስራ መጠን ወይም ዲዛይን ለመቀየር የሚሰጥ መደበኛ ትእዛዝ ነው።

ዓይነቶች:-
- ስራ መጨመር
- ስራ መቀነስ
- ዲዛይን መቀየር
- የእቃ አይነት መቀየር

ዋና ነጥቦች:-
- በመደበኛ ሁኔታ መፀደቅ አለበት
- የኮንትራቱ ዋጋ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል
- የጊዜ ማራዘሚያ ሊያስፈልግ ይችላል

ፎርሙላ:-New Contract Price = Original Price ± Variation Value

4.
ቦነስ (Bonus)

ትርጉም:-ቦነስ ማለት ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን ከተወሰነው ጊዜ በፊት ካጠናቀቀ የሚሰጥ ተጨማሪ ክፍያ ነው።

ዓላማ:-
- ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ
- የመዘግየት አደጋ እንዲቀንስ

ምሳሌ:-
Bonus = 40,000 Birr / day
ቀደም ብሎ 10 ቀን ካጠናቀቀ
Bonus = 40,000 × 10 = 400,000 Birr

5.
ፔናልቲ (Penalty / Liquidated Damage)

ትርጉም፦ፔናልቲ ማለት ኮንትራክተሩ ፕሮጀክቱን በተወሰነው ጊዜ ካልጨረሰ የሚቀነስ ገንዘብ ነው።

ዓላማ:-
- የባለቤቱን ኪሳራ ለመከላከል
- ኮንትራክተሮች በጊዜ እንዲጨርሱ

ፎርሙላ:-
Penalty = Contract Price × Penalty Rate × Delay Days

ምሳሌ:-
Contract Price = 50,000,000 Birr
Penalty Rate = 0.1%
Delay = 20 days
Penalty = 50,000,000 × 0.001 × 20
Penalty = 1,000,000 Birr

6.
የጊዜ ማራዘሚያ (Extension of Time – EOT)
ትርጉም:- የጊዜ ማራዘሚያ ማለት ኮንትራክተሩ በማይቆጣጠሩ ምክንያቶች ሲዘገይ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት ነው።

ምክንያቶች:-
- ከባድ ዝናብ
- ጎርፍ
- የዲዛይን ለውጥ
- የክፍያ መዘግየት
- የጥሬ እቃዎች እጥረት

7.
የዋጋ ለውጥ (Price Escalation)
ትርጉም:- የዋጋ ለውጥ ማለት የስራ እቃ፣ ሰራተኛ ወይም ነዳጅ ዋጋ ሲጨምር የኮንትራቱ ክፍያ መቀየር ነው።

ፎርሙላ:- Pn = Po × (a + b(Ln/Lo) + c(Mn/Mo) + d(Fn/Fo))

8.
ሪቴንሽን ገንዘብ (Retention Money)

ትርጉም:-ሪቴንሽን ገንዘብ ማለት ከኮንትራክተሩ ክፍያ ውስጥ የሚቀነስ ገንዘብ ሲሆን የስራ ጥራት ለማረጋገጥ ይጠቀማል።

በተለምዶ:-
- 5% – 10% ይቀነሳል
መመለም
- 50% ስራ ሲጠናቀቅ
- 50% ከ Defects Liability Period በኋላ

9. የጉድለት ኃላፊነት ጊዜ (Defects Liability Period)
ትርጉም:-ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ኮንትራክተሩ የሚታዩ ጉድለቶችን በራሱ ወጪ የሚያስተካክልበት ጊዜ ነው።

የተለመደ ጊዜ:-
- 6 ወር
- 12 ወር

ምሳሌ ጉድለቶች:-
- የኮንክሪት ስንጥቅ
- የውሃ ፍሳሽ
- የመንገድ መውደቅ

10. ፐርፎርማንስ ቦንድ (Performance Bond)

ትርጉም፦ፐርፎርማንስ ቦንድ ማለት ኮንትራክተሩ ስራውን እንደሚፈጽም የሚሰጥ የገንዘብ ዋስትና ነው።

በተለምዶ:-10% የኮንትራት ዋጋ

11. አድቫንስ ክፍያ (Advance Payment)
ትርጉም:- አድቫንስ ክፍያ ማለት ስራ ከመጀመሩ በፊት ለኮንትራክተሩ የሚሰጥ የመጀመሪያ ክፍያ ነው።

በተለምዶ
- 10% – 20% የኮንትራት ዋጋ

ዓላማ:-
- መሳሪያ ለመግዛት
- ሰራተኞችን ለመከፈል
- ስራ ለመጀመር

12. ኢንተሪም ክፍያ (Interim Payment Certificate – IPC)

ትርጉም፦ኢንተሪም ክፍያ ማለት በፕሮጀክት ሂደት ውስጥ ለተጠናቀቀ ስራ በየወሩ የሚሰጥ ክፍያ ነው።

ፎርሙላ:- Payment = Work Done − Retention − Previous Payments

13. የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment Certificate)

@etconp

2 comments

Ashenafi Yisak
Thanks
Ashenafi Yisak
Keep it up