‎👉ስራ አቁመዋል? የስንብት ክፍያ መብትዎንና አሰላሉን ያውቃሉ?

💫‎​ብዙዎቻችን ከስራ ስንሰናበት ስለሚኖረን "የስንብት ክፍያ" (Severance Pay) መብትና አሰላለፍ ግልጽ መረጃ ላይኖረን ይችላል።

🚧በአዲሱ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ (ቁጥር 1156/2011) እና በሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ላይ በመመስረት ዋና ዋና ነጥቦችን እነሆ፦
‎
⭐️‎​የስንብት ክፍያ ለማግኘት መሟላት ያለባቸው 3 ቅድመ ሁኔታዎች፡
‎
‎I. ​የሙከራ ጊዜን ማጠናቀቅ።
‎
‎II. ​በጡረታ ሕግ መሠረት የጡረታ አበል ለመቀበል ብቁ አለመሆን።
‎
‎III. ​የሥራ ውሉ በአዋጁ በተገለጹ ምክንያቶች መቋረጥ።
‎​
‎⚡️የስንብት ክፍያ የሚያስገኙ ምክንያቶች፡
‎
‎* ​ድርጅቱ በኪሳራ ወይም በሌላ ምክንያት በቋሚነት ሲዘጋ።
‎
‎* ​አሰሪው ከሕግ ውጪ ሰራተኛውን ሲያሰናብት።
‎
‎* ​በሰራተኛው ላይ የሚደርስ ድንገተኛ የአካል ጉዳት ወይም ሞት።
‎
‎* ​በአሰሪው ጥፋት (ለምሳሌ፦ ጾታዊ ጥቃት፣ ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ድርጊት) ሰራተኛው ሾል ሲለቅ።
‎
‎​🎲የስንብት ክፍያ መጠን እንዴት ይሰላል?
‎
⏺‎​ብዙውን ጊዜ ክፍያው የሚሰላው በወር ደሞዝ ቢሆንም፣ በሕጉ (አንቀጽ 40) መሠረት በትክክለኛው መንገድ ሲሰላ ግን ሰራተኛው የተሻለ ክፍያ ያገኛል።
‎
‎​1. የአሰላለፍ ቀመር፡
‎
‎* ​ለመጀመሪያው ዓመት፡ የ30 ቀን አማካይ የዕለት ደሞዝ።
‎
‎* ​ለቀጣይ ዓመታት፡ ለእያንዳንዱ ዓመት የመጀመሪያው ዓመት ክፍያ ሲሜ (1/3ኛ) እየታሰበ ይታከላል።
‎
‎​2. የዕለት ደሞዝ እንዴት ይፈለጋል?
‎
⏺‎​በወር 208 የሥራ ሰዓት እንዳለ ይታሰባል።
⏺የወር ደሞዝ ለ 208 ሲካፈል የአንድ ሰዓት ደሞዝ ይገኛል፤ እሱም በ 8 ሰዓት ሲባዛ የዕለት ደሞዝን ይሰጣል። ​ለምሳሌ፡ 9,000 ብር ደሞዝ የሚከፈለውና ለ 9 ዓመት የሰራ ሰራተኛ፤ በተለመደው አሰራር፡ 33,000 ብር ሊያገኝ ይችላል። ​በሕጉ መሠረት ሲሰላ፡ 38,076.5 ብር ያገኛል። (ልዩነቱ ከ 5,000 ብር በላይ ነው!)
‎
‎​🔰ክፍያውን የማይከለክሉ ነገሮች፦
‎
‎* ​ከፍተኛ ደሞዝ መከፈል፡ "ደሞዝህ ከፍተኛ ስለሆነ አይገባህም" የሚል ክርክር በሕግ ተቀባይነት የለውም።
‎
‎* ​ንብረት አለማስረከብ፡ ሰራተኛው ንብረት ባለማስረከቡ ብቻ ክፍያው ሊከለከል አይችልም፤ አሰሪው ንብረቱን ለማስመለስ ሌላ የሕግ መንገድ መጠቀም አለበት።
‎
⚡️‎ማስታወስ ያለብዎት፡
‎
⏺‎የፕሮቪደንት ፈንድ (Provident Fund) ተጠቃሚ ከሆኑ፣ ክፍያው ከስንብት ክፍያ ጋር ስለሚኖረው ተደራራቢነት ወይም ልዩነት ውልዎን ማየትና የሕግ ባለሙያ ማማከር ተገቢ ነው።
‎
‎⭐️የ YouTube ገፃችን ለመቀላቀል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp

1 comment

ኮንስትራክሽን ላይ ለሚደርስ አደጋ ኢንሹራንስ ህጉ ምን ይላል ?