አሳዛኝ ክስተት‼️

በኮልፌ የህንፃ መደርመስ አደጋ ተከሰተ‼️

በህዳር 9/2019 ዓ.ም. ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ፣ በአዲስ አበባ ኮልፌ፣ ቀራንዮ ወረዳ 03፣ ከግራር ወደ ስልጤ ሰፈር በሚወስደው መንገድ፣ ከኑር ካፌ ከፍ ብሎ በመሠራት ላይ የነበረ ህንፃ ተደርምሷል።

ህንፃው የመሬት ወለሉን ጨምሮ የመጀመሪያና ሁለተኛ ፎቆቹ ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት ውለው እንደነበር ተገልጿል።

በአደጋውም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በህንፃው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ስንት እንደሞቱ ወይም እንደተጎዱ እስካሁን እየተጣራ ነው።

ይህ አደጋ የግንባታ ጥራትና የቁጥጥር ሥርዓት ጉዳይን በአስቸኳይ እንድንመለከት ያሳስባል።

የግንባታ ደረጃና ደህንነት መስፈርቶችን የማያሟሉ ሥራዎች በተገቢው ሁኔታ መቆጣጠር አለባቸው።

@etconp

2 comments

Elshadaye Tesfaye
please give ur feedback & proffiessional Solution Idea and Recommandation.
Mebratu Debeb
Hi