👉የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ከዓመታት መቋረጥ በኋላ ዳግም ተጀመረ!

🚧በአዋሽ-ኮምቦልቻ-ሐራ ገበያ መስመር ላይ ተቋርጦ የነበረው የ1.7 ቢሊዮን ዶላር የባቡር መስመር ግንባታ፣ ከዓመታት መዘግየት በኋላ በይፋ ዳግም መጀመሩ ተገለጸ።

ይህ 392 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኤሌክትሪክ ባቡር መስመር፣ የአማራ ክልል ዋና ዋና የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከላትን ከአዲስ አበባ-ጂቡቲ የባቡር ኮሪደር ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ለሀገሪቱ የጭነትና የሰው ትራንስፖርት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

ግንባታው በ2015 እ.ኤ.አ. በቱርኩ "ያፒ መርከዚ" ኩባንያ የተጀመረ ቢሆንም፣ በኖቬምበር 2020 በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት መሠረተ ልማቶቹ ላይ ጉዳት ደርሶና ውሎች ተስተጓጉለው ሥራው ቆሞ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ በመሻሻሉ ሠራተኞችና መሣሪያዎች ወደ ሳይት የተመለሱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን የጥገና እና መልሶ ግንባታ ሥራው በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል።

@etconp

1 comment

Kassahun Alemu
By What contractor ?