👉የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ አቅራቢው ባውሚት ኦስትሪያ ወደ ኢትዮጵያ ገባ

💫በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ባውሚት ኦስትሪያ መካከል በነበረው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቃቸው የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ  ኮርፖሬሽኑና ባውሚት ኦስትሪያ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ስምምነት ፈጽመዋል።

ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ሚስተር ኤድዋርድ አርትነር ተፈራርመዋል፡፡

የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ እና የባውሚት አፍሪካና ኤዥያ ብቸኛ ወኪል የሆነው የካሳ ዲ አርጂላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሮላንድ ጃንሰን የጫካ ሳተላይት ከተማ ፕሮጀክትን፣ በአዲስ አበባ ከተማ እተከናወኑ ያሉትን ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ለማድረግ ያከናወነውን የቅድመ ዝግጅት ስራም ተዘዋውረው ተመልተዋል፡፡

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ሁለንተናዊ አመራር ሰጭነት ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ተምሳሌት ሀገር በመሆኗ በቤት ልማት  ዘርፍ በቴክኖሎጂ አቅርቦት ጠንካራ ተሳትፎ እንደሚያደርግም ነው የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ የገለጹት፡፡

ተዘዋውረው በተመለከቱት አስደናቂ አገራዊ የልማት ሥራና ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ለማድረግ በኮርፖሬሽኑ በኩል በተከናወኑት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መደሰታቸውን ገልጸው፣ የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ አቅርቦት በአጭር ጊዜ ለመፈጸም ስምምነት  ላይ ለመድረስ ኩባንያቸው መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

የ3D ተክኖሎጂ ቤትን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በአጭር ጊዜ በማቅረብ የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ከመሰረቱ እንደሚቀይረው ያላቸው እምነት የገልጹት ሚስተር ኤድዋርድ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ ለሚገነቡት ቤቶችን  ባውሚት ኦስትሪያ የገንዘብና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

የባውሚት ኦስትሪያ አፍሪካና የኢዥያ ወኪል ካሳ ዲ አርጅላ በአንድ ዓመት ውስጥ የ3D ኮንክሪት ቴክነኖሎጂን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም  ሚስተር ኤድዋርድ ተናግረዋል፡፡

የባውሚት ኦስትሪያ 3D ኮንክሪት ተክኖሎጂ አቅርቦትና ተከላ፣ የእውቀት ሽግግር እና ሥልጠና ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን  የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ የወቅቱ የከተሞች ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ከመሰረቱ ለመቅረፍ ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው፡፡

ቤት ከመገንባት ወደ ማምረት የሚያስችለንን የ3D ኮንክሪት ቴክኖሎጂን ትግበራን በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ ሙሉ ሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ ከባውሚት ኦስትሪያ ጋር እንደሚሠራም ተናግረዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ እና የአገራዊ ቤት ልማት እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነቱ ትልቅ ሚና እንሚኖረው አቶ ረሻድ ተናግረዋል፡፡

Via ኢንፍራኮን ሚዲያ


@etconp

1 comment

Elshadaye Tesfaye
ይህ ትልቅ እድል መሰረት መለወጥ አፈልጋለሁ ከእናነተ ጋር መስራት አችላለሁ በConcrete ሙያ ውስጥ ነው ምርጫቹ ካደረጋችሁ አብረን በንስራ ደስተኛ ነኝ!!! አመሰግናለሁ::