👉ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና መሠጠት ጀመረ
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ተገጣጣሚ ቤቶችን ከሚገነባ የግል ድርጅት ጋር በመተባበር ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና መሥጠት ጀምሯል።
የኢንስቲትዩቱ የሲቪል ፋካሊቲ ዲን ወ/ሮ ሰሎሜ ፋንታሁን በአገራችን ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ አጭር እድሜ ያለው ቢሆንም ሠፊ ፍላጎት እየተፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸው ይህንን ፍላጎት ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ለማስቀጠል ያለመ ስልጠና መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ስልጠናው 16 ለሚሆኑ አስልጣኞች የተዘጋጀ ሲሆን ለሁለት ወር የሚቆይ በተግባር እና በንድፈሃሳብ የተደገፈ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል።
ቤቶቹ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታንዳርድ የተዘጋጀላቸው መሆናቸውን የተገለፀ ሲሆን የዘንድሮ ተመራቂዎች የማህበረሰብ አገልግሎት የቤት ግንባታ ላይ የሚተገበር እንደሆነም ተገልጿል፤
መሠል ስልጠናዎች ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለማስረጽ እና ለሥራ ፈጠራ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረውም በስልጠናው ላይ ተብራርቷል፡፡
ሥራና ክህሎት ሚኒስትር
@etconp
We are called Asnakech Prefabricated Houses. We are currently giving training to instructors at TVET and for more information on the technology you can visit out telegram channel and subscribe using thus link https://t.me/AsnakechPrefabricatedHouses @manderas
Call on 0972-722272