👉በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው  ወጣቶች  ወደ  ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አመሩ

✅ዜጎች ደህንነትና ክብራቸው ተጠብቆ  ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ዘርፉን ሪፎርም ለማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡

✅ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በራሱ አቅም ያለማውን የኢትዮጵያ ሼል ገበያ መረጃ ስርዓት በመጠቀም አገልግሎቱን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች ሀገራችን የሁለትዮሽ ስምምነት  በፈፀመችባቸው ሀገራት ከሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች በስፋት ተጠቃሚ  ማድረግ ችሏል፡፡

✅ ምንም እንኳን በየዓመቱ ከሚፈጠረው የሥራ ዕድል ሰፊውን ቁጥር በሀገር ውስጥ የሚፈጠረው የሥራ ዕድል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በውጭ ሀገር ሼል ሥምሪቱ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ አንድ አማራጭ በተሠሩ ሥራዎች የሙያ ባለቤት የሆኑ ዜጎች  በውጭ ሀገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ላይ በመሰማራት ራሳቸውንና  ሀገራቸውን ተጠቃሚ የሚያደርጉበት ዕድል ተፈጥሯል፡፡

✅በዚሁ መሰረት በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው  ወጣቶች  ወደ  ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምርተዋል ።

✅ወጣቶቹ በተለያዩ የኮንስትራክሽን ሼል ሙያዎች የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን በቀጣይም  የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ለዜጎች አማራጭ ሆኖ ተገቢው ዝግጅት ተደርጓል፡፡

Via ሥራና ክህሎት ሚኒስትር

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp

1 comment

አሁንስ እንዴት ነው ይህንን እድል መጠቀም የምንችለው?