👉62.6 ቢሊየን ብር ውል የተገባለት የሚኤሶ - ድሬዳዋ ፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የጨረታ ሂደቱ ምን ይመስላል? 💫ከዓለም ባንክ ድህረገጽ ላይ ይፋ ከሆነው የአሸናፊ ድርጅት ማሳወቂያ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ፕሮጀክቱ በሁለት ሎት ተከፍሎ የተከናወነ ነው።
⏺ሎት 1 ላይ 5 ተጫራቾች የተሳተፉ ሲሆን 4 የቻይና እና አንድ የህንድ ድርጅቶች ናቸው።
🏗አሸናፊው ድርጅት ለዚህ ሎት 31.14 ቢሊየን ብር (172.9 ሚሊየን በዶላር እና 9.3 ቢሊየን በብር) ያቀረበ ሲሆን በሌሎች ተጫራቾች ከቀረቡት ዋጋዎች መካከል ከፍተኛው 39.1 ቢሊየን ብር መሆኑን ያሳያል።
🚧ሎት 2 ላይ 4 የቻይና ድርጅት የተሳተፉ ሲሆን አሸናፊው ድርጅት ለዚህ ሎት 31.4 ቢሊየን ብር (174.3 ሚሊየን በዶላር እና 9.4 ቢሊየን በብር) አቅርቧል።
⏺ለዚህ ሎት በሌሎች ተጫራቾች ከቀረበው ዋጋ ከፍተኛው 38.5 ቢሊየን ብር መሆኑን ያሳያል።
⏺የፕሮጀክቱ የውል ጊዜ አራት ዓመት ሆኖ ዲዛይንና ግንባታው (Design-Build) በስራ ተቋራጩ የሚከናወን መሆኑም ተጠቅሷል።
⏺ኮንትራቱ የtolling መሰረተ ልማቶች እና Intelligent Transportation System (ITS) አካቷል።
@etconp