👉62.6 ቢሊየን ብር ውል የተገባለት የሚኤሶ - ድሬዳዋ ፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የጨረታ ሂደቱ ምን ይመስላል?

💫ከዓለም ባንክ ድህረገጽ ላይ ይፋ ከሆነው የአሸናፊ ድርጅት ማሳወቂያ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ፕሮጀክቱ በሁለት ሎት ተከፍሎ የተከናወነ ነው።

⏺ሎት 1 ላይ 5 ተጫራቾች የተሳተፉ ሲሆን 4 የቻይና እና አንድ የህንድ ድርጅቶች ናቸው።

🏗አሸናፊው ድርጅት ለዚህ ሎት 31.14  ቢሊየን ብር (172.9 ሚሊየን በዶላር እና 9.3 ቢሊየን በብር) ያቀረበ ሲሆን በሌሎች ተጫራቾች ከቀረቡት  ዋጋዎች መካከል ከፍተኛው 39.1 ቢሊየን  ብር መሆኑን ያሳያል።

🚧ሎት 2 ላይ 4 የቻይና ድርጅት የተሳተፉ ሲሆን አሸናፊው ድርጅት ለዚህ ሎት 31.4 ቢሊየን ብር (174.3 ሚሊየን በዶላር እና 9.4 ቢሊየን በብር) አቅርቧል።

⏺ለዚህ ሎት በሌሎች ተጫራቾች ከቀረበው ዋጋ  ከፍተኛው 38.5 ቢሊየን  ብር መሆኑን ያሳያል።

⏺የፕሮጀክቱ የውል ጊዜ አራት ዓመት ሆኖ ዲዛይንና ግንባታው (Design-Build) በስራ ተቋራጩ የሚከናወን  መሆኑም ተጠቅሷል።

⏺ኮንትራቱ የtolling መሰረተ ልማቶች እና Intelligent Transportation System (ITS) አካቷል።

@etconp

1 comment

Yihenework Bezu
አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ካፓኒ ስም ቢገለፅ 🤔