👉ለቢሾፍቱ ኤርፖርት ግንባታ የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ስድስት ቢሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት ቃል መግባታቸው ታወቀ

🚧‎የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ አጠገብ አቡሴራ በተባለ አካባቢ ለሚያስገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት፣ የተለያዩ የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ስድስት ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ ቃል መግባታቸው ተገለጸ።
‎
⏺የአየር መንገድ ግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ወር በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም የተገኙ የተለያዩ አገሮች ፋይናንስ አቅራቢዎች ለፕሮጀክቱ ግንባታ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ ቃል ገብተዋል፡፡

⏺‎ለዓለም አቀፍ ኤርፖርቱ ግንባታ ዝርዝር የፉይናንስ ሞዴልን ያካተቱ የፕሮጀከት መረጃዎችን ያቀፉ ሰነዶች ብድር ማቅረብ ለሚችሉ አካላት መላኩን አየር መንገድ ግሩፑ ያስታወቀ ሲሆን፣ ለቢሾፍቱ ኤርፖርት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የሚያስፈልገው ወጪ 12.5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ መሆኑንና የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታውም እ.ኤ.አ. በ2030 ተጠናቆ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞች ያስተናግዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡

Via ሪፖርተር

@etconp

1 comment

Abe Man
Link endet enagegnalen