🌱 ስም ማቆላመጥ ?
•
ጥያቄ፡- ‘
ዐብዱላህ’ የሚለውን ስም ‘ዐቡድ’፣ ወይም ‘
ዐብዱራሕማን’ የሚለውን ‘ደሑም’ ብሎ ማቆላመጥ (ማሳነስ) እንዴት ይታያል? ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም?
•
መልስ፡- ይህ
ይፈቀዳል። ይህ የብዙ ሰዎች ልማድ ነው፤ እንዲያውም የኡለማዎች (ሊቃውንት) ጭምር። ስለዚህ ‘ዐብዱልዐዚዝን’ - ‘ዐዙዝ’፣ ‘ዐብዱልመጂድን’ - ‘መጁድ’ እያሉ ማቆላመጥ ይፈቀዳል።
ምክንያቱም እያቆላመጥክ (እያሳነስክ) ያለኸው የሰውየውን ስም ነው።
ክልክል የሆነው የአላህን ስሞች ማሳነስ ነው፤ ይህ በሊቃውንት ስምምነት (ኢጅማዕ) የተከለከለ ነው። ለምሳሌ ከአላህ ስሞች አንዱ የሆነውን ‘አል-ዐዚዝ’ የሚለውን ‘ዐዘይዝ’ (ለአላህ ተብሎ) ቢባል — አላህ ይጠብቀንና — ይህ በፍጹም አይፈቀድም። ነገር ግን የአላህ ባሪያዎችን ስም ማቆላመጥ (ማሳነስ) ይቻላል።
🌱 @TewhedandSuna