This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌱 ስም ማቆላመጥ ?

•ጥያቄ፡- ‘ዐብዱላህ’ የሚለውን ስም ‘ዐቡድ’፣ ወይም ‘ዐብዱራሕማን’ የሚለውን ‘ደሑም’ ብሎ ማቆላመጥ (ማሳነስ) እንዴት ይታያል? ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም?

•​መልስ፡- ይህ ይፈቀዳል። ይህ የብዙ ሰዎች ልማድ ነው፤ እንዲያውም የኡለማዎች (ሊቃውንት) ጭምር። ስለዚህ ‘ዐብዱልዐዚዝን’ - ‘ዐዙዝ’፣ ‘ዐብዱልመጂድን’ - ‘መጁድ’ እያሉ ማቆላመጥ ይፈቀዳል።

​ምክንያቱም እያቆላመጥክ (እያሳነስክ) ያለኸው የሰውየውን ስም ነው። ክልክል የሆነው የአላህን ስሞች ማሳነስ ነው፤ ይህ በሊቃውንት ስምምነት (ኢጅማዕ) የተከለከለ ነው። ለምሳሌ ከአላህ ስሞች አንዱ የሆነውን ‘አል-ዐዚዝ’ የሚለውን ‘ዐዘይዝ’ (ለአላህ ተብሎ) ቢባል — አላህ ይጠብቀንና — ይህ በፍጹም አይፈቀድም። ነገር ግን የአላህ ባሪያዎችን ስም ማቆላመጥ (ማሳነስ) ይቻላል።

🌱 @TewhedandSuna

1 comment

ለምሳሌ ኢላሂዬ ቢልስ እንዴት ይታያል