👉የኮንስትራሽን ዘርፉን ወደ ከፍታ የሚያሸጋግር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ ይፋ ሆነ

የኮንስትራሽን ዘርፉን ወደ ከፍታ ለማሸጋገር በፈረንጆቹ ከ2025 እስከ 2050 ድረስ የሚተገበር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ ይፋ ተደርጓል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዚህ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መፍጠር ያስልጋል።

በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ለመቆየት ተወዳዳሪነት እና ብቃት ወሳኝ በመሆኑ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ እና ወጪ ማጠናቀቅ አንዱ መገለጫ ሊሆን ይገባል።

አሰራሮችን ማዘመን ፣ቴክኖሎጂን መጠቀም፣ እና ዘመናዊ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓትን መከተል ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ህልውና እና አስተማማኝ እድገት ለማምጣት ወሳኝ ናቸው።

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለሀገራችን እድገት ጉልህ አስተዋጸኦ ሲያበረክት የቆየ እና በቀጠይም ማሳካት ለሚፈለገው ግብ የማይተካ ሚና ያለው ከመሆኑም ባሻገር መንገዶች ለማህበራዊ አገልግሎቶች ያላቸው ተደራሽነት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

ኢንዱስትሪው የሀገር ሥልጣኔ ማሳያ እንደመሆኑ ሥራዎችን በትብብር ማከናወን እንደሚገባ ተገልጿል።

Via ERA

@etconp

1 comment

great job.....