👉ማስታወቂያ ለአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጮች

🌟በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የግዥ ሥርዓት የመሳተፍ ዕድል!

ለተከበራችሁ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችና ሥራ ተቋራጮች

መስከረም  21 ቀን UNECA አዳራሽ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የግዥ ሥርዓት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሴሚናር ላይ ማኅበራችን በንቃት ተሳትፏል።

መድረኩ አገር ውስጥ የሚገኙ ተቋማት በዓለም አቀፉ ገበያ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሰፊ ዕድል ያመላከተ ነበር።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎች ከአነስተኛና መካከለኛ የገጠር ልማት ፕሮጀክቶች እስከ ከፍተኛ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ድረስ ለአገር ውስጥ ተቋማት ሰፊ የሥራ ዕድል የሚያቀርቡ በመሆኑ፣ ፍላጎቱ ያላችኹ የማኅበራችን አባላት የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎች በማሟላት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን።

📋 ተፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎች

1. ምዝገባ፦ በዩኤንጂኤም (UNGM - United Nations Global Marketplace) በሥራ ተቋራጭነት መመዝገብ፣

2. ሥነ-ምግባር፦ ዓለም አቀፍ የግዥና የሙያ ሥነ-ምግባር ደንቦችን ማሟላት፣

3. ብቃት፦ የተቀላጠፈና ጥራቱን የጠበቀ የፕሮጀክት አስተዳደር አቅም ማሳየት።

⏰ የማመልከቻ ጊዜ ገደብ
የመጨረሻ ቀን መስከረም 30 / October 10, 2026

🔗 የምዝገባ መረጃ እና ማመልከቻ ማድረሻ
ይህንን ዕድል በመጠቀም ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦
https://unicef-ethiopia-suppliers.com/

ለማንኛው እገዛና ጥያቄ: +251 98 477 7722

🔷 የኢትዮጵያ  የኮንስትራክሽን ሼል ተቋራጮች ማኅበር

@etconp

1 comment

Temesgen Tadiwos
ሠላም ይብዛላችሁ በዝህ ላይ ለመሣተፍ እፈልጋለው አንደንደ ኢንፎርሜሽን አካፍለኝ