አሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ 12.5 ቢሊዮን ዶላር የቢሾፍቱ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ውስጥ የአሜሪካ ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ደጅ እየጠናች ነው።

አሜሪካ በቢሾፍቱ እየተገነባ ባለው አዲሱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ውስጥ የአሜሪካ ኩባንያዎች ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየሰራች መሆኗን የአሜሪካ የንግድ መምሪያ ከፍተኛ ኃላፊ ማርክ ሚቼል ተናግረዋል።

ሚቼል እንዳሉት፣ ዋሽንግተን በፕሮጀክቱ ውስጥ የአሜሪካ ኩባንያዎች ተሳትፎ እንዲረጋገጥ " በቅርበት እየሰራች " ሲሆን፣ ይህም በአፍሪካ የመሠረተ ልማትና የኢንቨስትመንት ተፅዕኖ ለማሳደግ አሜሪካ ከቻይናና ከሌሎች ኃያላን ሀገራት ጋር እያደረገችው ያለው ፉክክር አካል መሆኑን አመልክተዋል።

እሳቸው ይህን ያሉት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም ወቅት በቪዲዮ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊዎችም ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።

ሚቼል የአሜሪካ ኩባንያዎች በፕሮጀክቱ ውስጥ በትክክል ምን ዓይነት ሚና እንደሚኖራቸው በይፋ ባይገልጹም፣ ትብብሩ ወደፊት በGE Aerospace ሞተሮች የሚንቀሳቀሱ ተጨማሪ የቦይንግ አውሮፕላኖች ግዥ ሊያመራ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚያዝያ ወር ተጨማሪ 6 የቦይንግ 787-9 Dreamliner አውሮፕላኖችን ለመግዛት ስምምነት የፈረመ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከታዘዡ 20 አውሮፕላኖች ተጨማሪ ነው።

ከወራት በፊት በቢሾፍቱ የተጀመረው እጅግ ግዙፉ ፕሮጀክት በ2030 ሲጠናቀቅ "የአፍሪካ ዱባይ" እንዲሆን ታቅዷል።

ከአበዳሪዎች አንዱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ለፕሮጀክቱ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን ከጠቅላላው ወጪ 8.7 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ማሰባሰብ ሂደትንም እየመራ ነው።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት በፕሮጀክቱ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን መግለጻቸውን ተናግረው ነበር።

በተጨማሪም፥ አሜሪካ ከኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኢንስቲትዩት ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ሚቼል ገልጸው፣ ይህም የአሜሪካ የAI ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ እና ወደ አፍሪካ ገበያ እንዲስፋፋ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን አስታውቀዋል።

Via ሮይተርስ

@etconp

1 comment

Abdulqehar Tassew
ምንም ተሳትፎ ሳያደርጉ አባይ በኛ ገንዘብ ተሰራ እንዳለው ጉረኛው ትራምኘ ነገም ሊጎሩሩብን ቢሆንስ? ይቅርብን በግብር እየጦዝን አይደለ? እኛው እናሰረዋለን!