የህንፃ ግንባታ የሚካሄድበት ሳይት አካባቢ አሮጌ መኪናዋን Park አድርጋ ውስጡ ተቀምጣለች።

በቅርብ ነበር ከመስተንግዶ ስራዋ የተባረረችው። ከስራዋም የተሰናበተችው ያለ በቂ ምክንያት ነበር። በ Austin Texas ውስጥ የምትኖረው ይህቺ ሴት ከስራዋ ስለተሰናበተችና የቤት ክራይ መክፈል ስላልቻለች መኪናዋ ውስጥ ነበር የምትኖረው። ታዲያ ህንፃ የሚገነባበት ሳይት አካባቢ አሮጌ መኪናዋን አቁማ ውላ ስታድር የተመለከተው የአንድ ህንፃ ፎርማን / ኢንጅነር ወደ እሷ ቀረበና - "ብዙ ጊዜ እዚህ ስፍራ ላይ አይሻለሁ ፤ ስራ ትፈልጊያለሽ..?" ብሎ ጠየቃት። እሷም ያለማመንታት "አዎ.." አለችው። ታዲያ በዚህ ሰአት ነበር የ Rubi Hernandez ህይወት ሙሉ ለሙሉ የተቀየረው። "ነገ በጠዋት ስራ ጀምሪ - በቀን 150 ዶላር ደሞዝ እከፍልሻለሁ.." ሲላት "እሺ.." ብላ ተስማማች። ከዚህ በፊት የቀን ስራ / የኮንስትራክሽን ስራ ሰርታ ስለማታውቅ እጇን እያመማትም ቢሆን ስራውን በደንብ ወጥራ ያዘች። የሳምንቱ መጨረሻ ላይ የደሞዝ ቀን ደረሰና ስራ ያስቀጠራት ኢንጅነር ደሞዟን ሰጥቷት - "እዚህ ካሉ የኮንስትራክሽን ሰራተኞች በላይ አንቺ ጠንካራ ነሽ.." ብሎ አበረታታት። ከ 6 ወር በኋላ በዛው ሳይት ብዙ ሙያዎችን ለመደች። በ 6 ወር ውስጥ ከለመደቻቸው ሙያዎች መካከል - Electric Installation ስራ፣ Framing እንዲሁም ሌሎች በርካታ የኮንስትራክሽን ሙያዎች ይገኙበታል። ከ 1 አመት በኋላ የ Construction License አወጣች። ከ 2 አመት በኋላ ደግሞ የራሷን የ Construction Company መሰረተች። Rubi Hernandez በአሁኑ ሰአት በአመት 10 ሚሊየን ዶላር ገቢ የሚያስገባ የ Construction Company ባለቤት ናት።

Via Fraol

@etconp

2 comments

የሚአበረታታ ነገር ነው፣እውነት አመሰጊናላው
S Samuel
ኢትዮጲያ ውስጥ license አውጥተህ
አመታዊ ግብር እየከፈልክ
ምንም እንኳን ወጥ አሰራር ባይኖርም project ለማግኘት እየሞከርን ነው