🏗️ጃንቦ Vs ጀንቦሮ: የሪል እስቴት የንግድ ስም ውዝግብ

​"ጀንቦሮ ሪል እስቴት" (Jenboro Real Estate) የተሰኘ የንግድ ስም በሕጋዊ መንገድ ለማስመዝገብ ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ማመልከቻ ማቅረቡን ተከትሎ፣ ከ "ጃምቦ ሪል እስቴት" ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

​በጉዳዩ ዙሪያ የጃምቦ ሪል እስቴት የድርጅቱ ኃላፊዎች የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦

​የፍርድ ቤት ክስ ባለበት ሁኔታ: በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድና ኢንቨስትመንት ችሎት ተይዞ በነበረው ክስ ላይ ገና ውሳኔ ባልተሰጠበት ወቅት፣ ተመሳሳይ ስም ይዞ ለመመዝገብ መሞከሩ ጉዳዩን የበለጠ እንደሚያወሳስበው ገልጸዋል።
​የቀን መሠረትና ምዝገባ: ድርጅታቸው ስሙን በሕጋዊ መንገድ ያስመዘገበውና የመጠቀሚያ ፈቃድ ያገኘው በ2007 ዓ.ም እና በ2011 ዓ.ም ባደረጋቸው ተከታታይ ምዝገባዎች መሆኑን አስታውሰዋል።

​የደንበኞች ብዥታ: የስም መመሳሰሉ በደንበኞችና በማኅበረሰቡ ዘንድ ሰፊ ግራ መጋባትን (Consumer Confusion) እየፈጠረ በመሆኑ የሕግ ጥበቃው አብሳሪ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

​🌐የብራንድ ጥበቃ እና የሕግ አውድ
​በዓለም አቀፍ የአእምሯዊ ንብረት ሕግ (WIPO) እና በኢትዮጵያ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ መሠረት፣ ተመሳሳይ ስሞችን በመጠቀም ደንበኞችን ማደናገር እና አላስፈላጊ የገበያ ውድድር መፍጠር በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ተቋማት የፈጠራና የብራንድ መብቶቻቸውን በሕግ ማስከበር እንዳለባቸው የንግድ ውድድር ደንቦች ያሳስባሉ።

​⚠️ ቀጣይ እርምጃ: የጃንቦ ሪል እስቴት ኃላፊዎች፣ ተከሳሹ ድርጅት ተመሳሳይ ስያሜ ለማስመዝገብ ያቀረበውን ጥያቄ በመቃወም ዝርዝር ሕጋዊ ማስረጃዎችን ለባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

​የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የቀረበውን የተቃውሞ አቤቱታ እና የስም ምዝገባ ጥያቄ መርምሮ በቀጣይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@etconp

1 comment

Are they really the same?🤔🤔